
አዲስ አበባ: ሚያዝያ 18/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን እና የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኤልሻዳይ ኢንተርቴመንት ጋር በመቀናጀት ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል የገቢ ማሰባሰብ መርሃ ግብር ይፋ አድርገዋል።
የማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣቶች ተሳትፎና ንቅናቄ ተጠባባቂ ዳይሬክተር ሀብታሙ ከበደ ወጣቶች ሀገርና ሕዝብ ለገጠማቸው ችግር መፍትሔ ለመፈለግ ክፍተኛ ጥረትና ተጋድሎ እያደረጉ እንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡ አቶ ሀብታሙ አሁንም እንደ ሀገር ያለውን ችግር ለመፍታት በየአደረጃጀቶች የተለያዩ ሥራዎች እየተሠሩ እንደሆነ ነው ያስገነዘቡት።
ከሚያዝያ 1/2014 ዓ.ም እስከ ሰኔ 30/2014 ዓ.ም ባለው ጊዜ በተለይም በጦርነትና ድርቅ የተጎዱ ወገኖችን ለመደገፍ 500 ሚሊዮን ብር ለማሰባሰብ የ3 ወር ተግባር ይፋ ማድረጋቸውን ነው የተናገሩት።
የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌደሬሽን ምክትል ፕሬዝደንት ፅጌሬዳ ዘውዱ ወጣቱ የከፈለውን አኩሪ መስዋእትነት እውቅና በመስጠት የልማትና ሰላም ጠበቃነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል እንደሚሠሩ ገልጸዋል። የ3 ወር መርሃ ግብር የሀብት ማሰባሰብ ሂደቱን ሲገልጹም።-
በኢትዮ ቴሌኮም አጭር የጽሑፍ መልዕክት በማዘጋጀት በሚካሄደው ድጋፍ የዕጣ እድል እንዲኖረው ይደረጋል።
በሁሉም ክልሎች ሩጫዎች ይካሄዳሉ፡፡ በተመረጡ ከተሞች የሙዚቃ ኮንሰርቶች ይዘጋጃሉ፡፡
በየደረጃው ኤግዚቢሽኖችና የስፖርት ቶርናመንቶች ይካሄዳሉ፡፡
የሀብት ማሰባሰብ መርሃ ግብሩ በወጣቶች መሪ አስተባባሪነት በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ይካሄዳል፡፡
የሀብት ማሰባሰብ መርሃ ግብሩ ከሚያዝያ እስከ ሰኔ 2014 ዓ.ም የሚካሄድ ይሆናል፡፡
መርሃ ግብሩን በማስተባበር የሚሳተፉ አካላት በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ የወጣት አደረጃጀቶች መሪነት እና በበጎ ፈቃኛ ወጣቶች አስተባባሪነት የሚካሄድ ይሆናል፡፡
በሁሉም መርሃ ግብሮች ላይ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊ እና የውጭ ሀገር ዜጎች ሊሳተፉ ይችላሉ ተብሏል፡፡
የኤልሻዳይ ኢንተርቴመንትና መልቲ ሚዲያን የወከለው ኤልሻዳይ አሳዬ ሀገርኛ ባሕል እሴትና ክዋኔዎችን በመጠቀም ሀብት ማሰባሰብና መደገፍ ትልቁ ዓላማቸው እንደሆነ ነው የገለጸው።
‟በተለይ መላው ኢትዮጵያዊያና የኢትዮጵያ ወዳጆች ሁላችን በበዓል ውስጥ ሆነን ባለንበት በዚህ ወቅት በርካቶች በምን ሁነት ውስጥ እንዳሉ በማሰብና ጉዳታቸውን በመረዳት በእውቀታችን፣ በገንዘባችንና በጉልበታችን እንድንደግፍ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ” ብሏል። ትናንት ወተት እንደ ውኃ ቀድቶ ጠጡልኝ ሲል የነበረ ሕዝብ ዛሬ ውኃ አጥቶ በስቃይ ውስጥ በመሆኑ ይህን በመገንዘብ መደገፍ እንደሚገባ ነው ያስገነዘበው፡፡
ዘጋቢ፡-እንዳልካቸው አባቡ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/