በኮሜዲያን እሸቱ መለሰ አስተባባሪነት ከ 2 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁስ በችግር ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ ተደረገ።

266

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 18/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ኮሜዲያን እሸቱ መለሰ “የድጋፉ መነሻ ከአባታችን አቡነ በርናባስ ጥሪ ተደርጎልን ሰቆጣ መጥተን የተፈናቀሉ ወገኖችን ያሉበትን ችግር ካዬን በኋላ የአባታችን መልእክት በማስተላለፍ ለህዝብ ባቀረብነው የድጋፍ ጥሪ መሰረት ነው” ብሏል።

የመጣው ደጋፍም ከግለሰቦችና ድርጅቶች የተገኘ ዱቄት፣ ዘይት፣ ብርድ ልብሶች፣ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ፣ አልባሳት እና ሌሎችን ጨምሮ መሆኑን ኮሜዲያን እሸቱ አስታውቋል። በአጭር ቀናት ውስጥ ድጋፉ ለተጠቃሚዎች እንዲደርስ የትራንስፖርት እና ሌሎች ወጭዎችን ለደገፋቸው ለዋግ ልማት ማኀበር ምስጋና አቅርቧል።

የዋግ ልማት ማኅበር ዋና ዳይሬክተር አቶ አምላኩ አበበ የልማት ማኅበሩ በተፈጠረው ችግር መክንያት በርካታ ድጋፎችን በማሰባሰብ እና ድጋፍ ለሚያደርጉ ግለሰቦች መረጃ በመስጠት የተፈናቃይ ወገኖችን ችግር ለመቅረፍ ጥረት እያደረገ ያለ የሕዝብ ማኅበር መሆኑን ገልጸዋል።

አቶ አምላኩ አበበ አያይዘው እንደገለፁት ኮሜድያን እሸቱ መሰለ በአካባቢያችን ያለዉን መሠረታዊ ችግር በተገቢው መንገድ ከተረዱ በኋላ የተፈናቀሉ ወገኖቻችን ለመርዳት ባደረጉት ጥረት 136 ኩ/ል ዱቄት፣ 740 ሊትር ዘይት፣ 200 ብርድ ልብስ፣ 267 የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ፣ 40 ኩ/ል አልባሳት እና ሌሎችን ጨምሮ ያመጡትን ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ ተረክበን ባሉበት ለተጠቃሚዎች አሰራጭተናል ብለዋል።

አቶ አምላኩ አበበ የአካባቢያችን መሰረታዊ ችግር በሚዲያ አዉጥተዉ፣ ሚዲያቸዉን ተጠቅመው፣ ድጋፍ አሰባስበው እና በአካል እዚህ ተገኝተው ድጋፉን ለእናቶችና ህፃናት፣ ለአካል ጉዳተኞችና ለአረጋውያን ባሉበት ማሰራጨት መቻሉ ኮሜዲያን እሸቱ ያከናወነው ተግባር የሕዝብ ወገንተኝነት ያሳየበት ትልቅ ሥራ ነው ብለዋል። ድጋፉን ላደረጉ ወገኖች በሙሉ በዋግ ልማት ማኅበር እና በተፈናቃይ ወገኖች ስም ምስጋና አቅርበዋል።

በዓለም ዙሪያ ያላችሁ ወገኖች በክርስቶስ ትንሣኤ የምታምኑ እና የእምነቱ ተከታይ ለሆናችሁ በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ ያሉት ደግሞ የዋግ ኽምራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል አቡነ በርናባስ ናቸው። በዓሉ ለእምነቱ ተከታዬች የነፃነት፣ የሰላም፣ የፍቅር እና የደስታ በዓል መሆኑንም ገልጸዋል።

የተደረገውን ጥሪ ሰምታችሁ ወገናችሁን ለመደገፍ ያደረጋችሁት ተሳትፎ ርህራሄና አንድነታችሁን የሚገልፅ በመሆኑ ለሚዲያው አካላትና ድጋፍ ላደረጉ ወገኖች በአንድነት ልትመሰገኑ ይገባልም ብለዋል።

አቡነ በርናባስ እንደገለጹት ኮሜዲያን እሸቱ መሰለ በከተማችን ያለዉን ችግር አይቶና ተረድቶ በችግር ውሰጥ ያለውን ሕዝብ ለማገዝ አቅሙ በፈቀደው መጠን ባደረገው እንቅስቃሴ ምግብ ነክና ሌሎች የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስን ድጋፍ አሰባሰቦ ያመጣቸውን ንብረቶች ተረክበናል ለተረጅዎችም በቀጥታ አሰራጭተናል በመሆኑም ላደረጋችሁት በጎ ሥራ አግዛብሔር ለሁላቹሁም ዋጋችሁን ይክፈላችሁ ብለዋል። መረጃው የዋግኽምራ ኮምዩኒኬሽን ነው

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleበኩር ጋዜጣ ሚያዝያ 17/2014 ዓ.ም ዕትም
Next articleʺጊዜ ያደከማቸው የሚያጠግቡ ሕብስቶች፣የሀገር በረከቶች”