የአማራ ክልል መሥተዳድር ምክር ቤት ከሦስት ሺህ በላይ የሕግ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ ወሰነ።

161

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 15/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ኀላፊ አቶ ገረመው ገብረ ጻዲቅ በሰጡት መግለጫ የትንሣኤ እና የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ የክልሉ መሥተዳድር ምክር ቤት 3 ሺህ 141 የሕግ ታራሚዎችን በይቅርታ እንዲፈቱ ወስኗል ብለዋል።

በይቅርታ ከተፈቱት መካከል 3 ሺህ 85 ወንድ ታራሚዎች ሲኾኑ 56ቱ ደግሞ ሴቶች ናቸው ተብሏል።

በይቅርታ መመሪያው መሠረት ከ10 ዓመት በላይ በሚያስቀጣ የሙስና ወንጀል ፍርደኞች፣ በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ አስገድዶ መድፈር፣ በመሠረተልማት ውድመትና ዘረፋ ላይ የተከሰሱ ፍርደኞች በይቅርታ ተጠቃሚነቱ አልተካተቱም።

በሌላ በኩል ከዚህ ቀደም ለ23 ታራሚዎች ተሰጥቶ የነበረው ይቅርታ ተሰርዟል ብለዋል።

ይቅርታ ተጠቃሚነታቸው የተሰረዘባቸው ከማረሚያ ቤት ከወጡ በኋላ በሌላ የወንጀል ድርጊት ተሳታፊ ኾነው በመገኘታቸው መኾኑን አንስተዋል።

በይቅርታ የተፈቱ ታራሚዎች የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥና ፍትሕ እንዲሰፍን የበኩላቸውን መወጣት ይገባቸዋል ሲሉ አሳስበዋል።

ዘጋቢ:- ጋሻው አደመ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

Previous article“እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ!” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next articleʺጎለጎታን አስደንጋጭ ድምጽ አናወጻት፣ ዓለምን ብርሃን መላት”