የትንሣኤ በዓልን አንድነትን በማጠናከር እና ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም በመሥራት ማክበር እንደሚገባ የሃይማኖት አባቶች አሳሰቡ።

97

አዲስ አበባ : ሚያዝያ 15/2014 ዓ.ም (አሚኮ) “የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓልን ስናከብር አንድነታችንን በማጠናከር እና የኢትዮጵያን ዘላቂ ሰላም ለማስፈን በተግባር በመሥራት ሊኾን ይገባል” ሲሉ የሃይማኖት አባቶች አሳስበዋል፡፡

በክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ በነገው ዕለት የሚከበረውን የትንሣኤ በዓል በማስመልከት የሃይማኖት አባቶቹ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

“የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ የሰው ልጅ ሐጢያት የተሰረየበት ፣ ፍቅር የተገኘበት እንዲሁም ደኅንነት የተጎናፀፈበት ነው” ብለዋል፡፡

በዓሉን በተለያየ ምክንያት ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን በመደገፍ እና በመንከባከብ ማሳለፍ እንደሚገባም የሃይማኖት አባቶቹ አሳስበዋል፡፡

በኢትዮጵያ እየተስተዋሉ የሚገኙ የሰላም መደፍረሶች ዋጋ እያስከፈሉ ነው፤ ይህም አስቸኳይ መፍትሔ ሊያገኝ ይገባልም ብለዋል፡፡

እንደ ኢቢሲ ዘገባ ሕዝበ ክርስቲያኑም በመላ ሀገሪቱ ሰላም እንዲሰፍን ጥረቱን እንዲያጠናክር የሃይማኖት አባቶቹ ጠይቀዋል፡፡

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“ብዙዎች ሀገራችንን ለማገልገል እና ታላቋን ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ ሲሉ መስዋእትነት ከፍለዋል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next article“እነኾ ሲኦል ተጨነቀች፣ በግዞት የያዘቻቸውን ነብሳት ተነጠቀች”