የትንሣኤ በዓልን የተቸገሩ ወገኖችን በመጎብኘት ማክበር እንደሚገባ ብፁዕ አቡነ ሚካኤል አሳሰቡ፡፡

257

ደብረ ታቦር : ሚያዝያ 15/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ሕዝበ ክርስቲያኑ የትንሣኤ በዓልን ሲያከብር የተቸገሩ ወገኖችን በመጎብኘት ጭምር ሊኾን እንደሚገባ የደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ሚካኤል አሳስበዋል፡፡

ብጹዕነታቸው የትንሣኤ በዓልን አስመልክተው ቃለ ቡራኬ ሰጥተዋል፡፡ የትንሣኤ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅ ለማዳን ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከድንግል ማርያም ተወልዶ 33 ዓመት በምድር ላይ ተመላልሶ አስተምሮና በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ክቡር ስጋውን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ ድኅነትን ያጎናጸፈበት መኾኑን አብራርተዋል፡፡

ላለፉት ሁለት ወራት ፈጣሪያቸው የጾመውን ጾም ሲጾሙ የቆዩት የእምነቱ ተከታዮች ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ፈንቅሎ የተነሳበትን የትንሣኤ በዓል በቤተክርስቲያንና በቤታቸው በድምቀት ያከብራሉ፡፡

በዓሉን ምክንያት በማድረግም የደቡብ ጎንደር ሐገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብጹዕ አቡነ ሚካኤል ለምዕመናንና ለመላው ኢትዮጵያውያን ቃለ ቡራኬ ሰጥተዋል፡፡

”የትንሣኤ በዓልን የምናከብረው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተነስቷል ብለን ከማመስገን ባሻገር እኛም ከእርሱ ጋር ተነስተናል፤ የትንሣኤ ልጆች ነን ብለን በማመን ነው” ያሉት ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ምዕመናን በዓሉን ሲያከብሩ የተቸገሩ ወገኖችን በመጎብኘት ጭምር እንዲኾን አሳስበዋል፡፡

ብጹእነታቸው በዓሉ ሲከበር ኢትዮጵያ ያለባት የሰላም እጦት እንዲቀረፍላት መጸለይ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

ዘጋቢ፡-ዋሴ ባየ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየሽብር ጥቃት ለመፈፀም ሲዘጋጁ የነበሩ 34 የአልሸባብ አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ
Next article“ብዙዎች ሀገራችንን ለማገልገል እና ታላቋን ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ ሲሉ መስዋእትነት ከፍለዋል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)