የዘንድሮ የበዓል ገበያ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ማሳየቱን የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

234

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 14/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በባሕር ዳር ከተማ የበዓል ገበያን አሚኮ ተዟዙሮ ቃኝቷል፡፡ የዶሮ፣ የበግ፣ የፍየል እና የከብት ዋጋ ካባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ መታዬቱን ሸማቾች ተናግረዋል፡፡
የአሚኮ የጋዜጠኞች ቡድን በባሕር ዳር ዋና ዋና የእንስሳት ገበያ በመዘዋወር ባደረገው ቅኝት በሁሉም የእንስሳት ዋጋ ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ መኖሩን ተመልክቷል።
የበግ ነጋዴ የኾኑት አማረ ነጋሽ በባለፈው ዓመት 8 ሺህ ብር ሲሸጥ የነበረው የአንድ በግ ዋጋ በዚህ ዓመት ወደ 11 ሺህ ብር ከፍ ማለቱን ተናግረዋል።

አቶ አወቀ መኮንን ለበዓል የሚሆን በግ ሊገዙ በገበያ ውስጥ ሲዘዋወሩ ነበር ያገኘናቸው። ከባለፈው ዓመት 2 ሺህ ብር ጨምረው እንደገዙም ተናግረዋል።
ሌላው የአሚኮ የጋዜጠኞች ቡድን ተዘዋውሮ ምልከታ ያደረገው የከብት ገበያን ነው። የከብት ነጋዴ የኾኑት ምትኬ ደረስ ዘንድሮ የከብት ዋጋ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪን ማሳየቱን ተናግረዋል። “በባለፈው ዓመት 40 ሺህ ብር ሲሸጥ የነበረው የአንድ ከብት ዋጋ ዘንድሮ እስከ 70 ሺህ ብር እየተሸጠ ነው” ብለዋል።

አቶ ብርሃኑ አንዳርጌም የዘንድሮ የከብት ዋጋ በጣም የተጋነነ መኾኑን ተናግረዋል። ከባለፈው ዓመት አንጻር ሲታይ በአንድ ከብት ላይ 50 በመቶ መጨመሩን ገልጸዋል።
የአሚኮ የጋዜጠኞች ቡድን በዶሮ ገበያ በመገኘትም የገበያውን ሁኔታ ተመልክቷል። ወይዘሮ በላይነሽ ታያቸው አንድ ዶሮ ለመግዛት 400 ብር ይዘው ወደ ገበያው ማቅናታቸውን ነግረውናል። ይሁን እንጂ የሚፈልጉትን ዶሮ 600 ብር ስለተባሉ ለመግዛት መቸገራቸውን ገልጸዋል። የዶሮ ነጋዴ የኾነው ወተቱ አትንኩት ከባለፈው ዓመት በተመሳሳይ ወቅት ሲታይ በአንድ ዶሮ ላይ 200 ብር መጨመሩን ነው የተናገረው።
ዘጋቢ:- ቡሩክ ተሾመ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleበወቅታዊ ሀገራዊ የደኅንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በመምከር፣ የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤቱ የሰጠው መግለጫ ።
Next article“ጌታችን ተመረመረ ዲያቢሎስ ታሰረ!”