
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 14/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጆችን የእዳ ደብዳቤ ይቀድ ዘንድ የእግዚአብሔር ልጅነታቸውን በደሙ ያጸና ዘንድ በእለተ አርብ የደረሰበትን መንገላታት በአጭሩ ታላቁ ቅዱስ መጽሐፍን ገለጥ አድርገን እንመልከት ፡- (ማቴ. 27÷27-31)
👉ሐሙስ ለአርብ አጥቢያ ለሊቱን ከ12ቱ ደቀ መዛሙርት አንዱ በኾነው በይሁዳ መሪነት ታግዘው ከያዙት በኃላ እያንገላቱት ወደ ሐና ወሰዱት፡፡
👉ሐና ከፊት እየመራ እየደበደቡ ወደ ሊቀ ካህናቱ ቀያፋ ቀጥሎም ወደ ጲላጦስ ወሰዱት፡፡
👉ከጲላጦስ ወደ ወደ ሔሮድስ በማመላለስ እንዲንገላታ ተደርጓል፡፡
👉በሂደቱም እየሰደቡትና እየዛቱበት ፊቱን በጥፊ ራሱን ደግሞ በዱላ ይመቱ አሰቃይተውታል፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰውልጆች ነጻ መውጣት ሲል በዕለተ ዓርብ ከሦስት እስከ ዘጠኝ ሰዓት የተቀበላቸው መከራዎች በጥቂቱ ስንቃኝ፡-
👉በጅራፍ ተገርፎአል፡፡
👉መስቀሉን ተሸክሞ በቀራንዮ ተራራ እየወደቀ እየተነሣ ተጉዟል፡፡
👉የገዢው የጲላጦስ ወታደሮችም እያዳፉት፣ ርኩስ ምራቃቸውንም እየተፉበትና እያፌዙበት ወደ ተራራው እንዲወጣ ተደርጎአል፡፡
👉የነቢያት ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ልብሱን ገፈው ከለሜዳ አልበሰውታል፡፡
👉በልብሱም ላይ ዕጣ ተጣጥለው ተካፍለውታል፡፡
👉የእሾህ አክሊል ጉንጉን በራሱ ላይ በማድረግ የሰማይና የምድር ንጉሥ እያሉ ተሳልቀዋል፡፡
👉ጎኑን በጦር ወግተውታል፡፡
👉እጆቹን እና እግሮቹን በ5 ችንካሮች ቸንክረው በመስቀል ላይ ሰቅለውታል፡፡
በመስቀል ላይ እያለ ከተናገራቸው ውስጥ፡-
👉እየበደሉት እሱ ግን ‹‹አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁትምና ይቅር በላቸው›› ይል ነበር፡፡
👉 ‹‹እነሆ ሁሉም ነገር ተፈጸመ››
የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ፈሪሳውያን በክርስቶስ ላይ ያቀረቡት መሠረተ ቢስ ክስና ውንጀላ፡-
👉ለቄሳር ግብር መክፈል አይገባም በማለት አስተምሮል፡፡
👉 ዕለተ ሰንበትን ሽሮአል፡፡
👉ራሱንም ከእግዚአብሔር ጋር አስተካክሏል የሚሉ ናቸው፡፡
የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ፈሪሳውያን በክርስቶስ ላይ ያቀረቡትን መሠረተ ቢስ ክስና ውንጀላ ለማጽናት የሄዱበት እርቀት፡-
👉በሐሰት የሚመሰክሩ ምስክሮችን በገንዘብ አባብለውና አደራጅተው አስመሰከሩ፡
👉በርባን የተባለው ወንጀለኛ እንዲፈታ ንጹኸ ባሕሪ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን እንዲሰቅለው ገዥው ጲላጦስ ልመና አቅርበዋል፡፡
👉 የገዥው ጲላጦስ ባለቤት በሕልም ተረድታ እጁን በጻድቅና ንጹሕ ሰው ደም እንዳያስገባ ስለመከረችው ‹‹እኔ ከዚህ ሰው ደም ንጹሕ ነኝ›› በማለት እጁን ከታጠበ በኋላ አሳልፎ ሰጣቸው፡፡
👉 ገዥው ጲላጦስ ንጹህ መኾኑን እያወቀ ወንበሩን ለማጽናት በፍርድ ወንበር ላይ ተቀምጦ የሰጠው የተዛባ ፍርድ ለትምህርት ይኾን ዘንድ ሲታወስ ይኖራል፡፡
👉የኢየሱስ የስቅለት ውጣ ውረድ ለእውነት መቆምን፣ ከተዛባ ፍርድ መቆጠብን፣ ከሐሰት ምስክርነት ራሰን መጠበቅን፣ እስከመጨረሻው መጽናትን፣ ምልጃን፣ እስከሞት የሚያደርስ ፍቅርን እንማርበት ዘንድ እነኾ አብነት ኾኖ ዛሬም ዘልቋል፡፡
በምሥጋናው ብርሃኔ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/