የህማማቱ ቀናት።

270

ባሕር ዳር: ሚያዝያ14/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የታላቁ ሁዳዴ ፆም መገባደጃ ሳምንት ሰሞነ ህማማት ይባላል፡፡ግሪካውያን ክርስቲያኖች ደግሞ ታላቁ ሳምንት ይሉታል፡፡ ጌታ ከተስፋዋ ምድር እስራኤል ከቤተ ፋጌ ወደ እየሩሳሌም አደባባይ ትህትናንበተግባር በማስተማር በአህያ መጥቷል፡፡

ደቅመዛሙርቱም በዘንባባ ተቀብለውታል፡፡ ዘንባባ የተስፋ እና የጌታ ዘላለማዊ ስልጣን እንደማሳያ ምልክት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

ከፋሲካ በፊት ያለው እሑድ ሆሳዕና ይባላል፡፡ በአርማይክ (በእብራይሰጥ) ሆሳዕና ‹‹አቤቱ አሁን አድን አሊያም መድኃኒት›› እንደ ማለት ይተረጎማል፡፡

ታዲያ ከሆሳዕና እስከ ፋሲካ ያሉት ቀናት ደግሞ የጌታ ህመም፣ የኦሪቱ የአዳም ሲቃይ የሚታወስበት ሳምንት በመሆኑ የህመም ሳምንት (ሰሞነ ህማማት) ይባላል፡፡ በሰሞነ ህማማት በየቀናቱ ጌታ የተለያዩ ተግባራትን ከውኖባቸዋልና ቀናቱም የራሳቸው ስያሜ አላቸው፡፡

ሰኞ፡- መርገመ በለስ ወይም አንጽሆተ ቤተ መቅደስ ትባላለች፡፡ምክንያቱም ጌታ በዕለተ ሰኞ የበለስ ቅጠልን ተመልክቶ ምንም ፍሬ ባለማግኘቱ ካሁን ጀምሮ ለዘላለም ምንም ፍሬ ካንቺ አይበላ ብሎ የረገመበትን ቀን ነው፡፡ ማቴ 11፣14
በዚሁ ዕለት ቤተ መቅደስም ንፁህ እንዲሆን ያደረገበት ቀን በመሆኑ አንጽሆተ ቤተ መቅደስ ትባላለች ፡፡ ማቴ21፣13

ማክሰኞ፡- የጥያቄ ቀን ወይም የትምህርት ቀን ትባላለች፡፡
ጌታ የሰው ልጅ ስልጣን ሲሰጥ በምን ስልጣንህ ይህን ታደርጋለህ ተብሎ በፈሪሳውያን ተጠይቋል፡፡ ማቴ 21፣23 ለዚህም የጥያቄ ቀን ይባላል፡፡

– በዚህ ቀንም ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተ መቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረ የትምህርት ቀንም ይባላል ሉቃ 21፣28

ረቡዕ፡- ምክር አይሁድ፣
የመልካም ማዕዛ ቀን ይባላል፡፡
እለቱ የአይሁድ ሊቀካህናት እና ጽሐፍተ ፈሪሳውያን ጌታን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው የመከሩበት ዕለት ነው፡፡ ሉቃ 22፣1
ባለሽቶዋ ማርያም ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ የአልባጥሮስ ሽቶ በጌታ ራስ ላይ አርከፍክፋለች፡፡ ለዚህም የመልካም ማዕዛ ቀን ይባላል፡፡ ማቴ 26፣6
በዚህ ዕለት ማርያም በይቅርታ በጌታ እግር ተንበርክካ ለሐጢያቷ አልቅሳለች፡፡ለዚህም የእንባ ቀን ይባላል፡፡ ማር14፣9

ሐሙስ፡- ጸሎተ ሐሙስ፣ የሐዲስ ኪዳኗ ሐሙስ፣ የነፃነት ሐሙስ ትባላለች፡፡ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለአይሁዳዊያን ተላልፎ ከመስጠቱ በፊት በጌተሰማኔ አትክልት ቦታ ሲፀልይ አድሯልና፡፡ ማቴ 26፣31፡፡
ጌታ የደቀ መዘሙርቱን እግር በትህትና ያጠበትም ቀን ነው። ዮሐ13፣3
ሉቃ 22፣2ዐ የሰው ልጅ ያጣውን ክብር የተመለሰበትም ቀን ነው፡፡ ዮሐ15፣15

ዓርብ፡- ስቅለተ ዓርብ ይባላል፡፡

ጌታ የወንጀለኛ መቅጫ የነበረውን መስቀል መዳኛ ለማድረግ የተሰቀለበት ዕለት በመሆኑ ማቴ 27፣35

ቅደሜ፡- ቅደም ስዑር፣ ለምለሚቱ ቅዳሜ ወይም ቅዱሷ ቅዳሜ ትባላለች፡፡
ከድሮው በተለየ ቅዳሜ የፆም ቀን በመሆኗ ቅደመ ስዑር (የተሻረችው ቅዳሜ) ትባላለች፡፡

በዚህተ ዕለት ካህናቱ ለምዕመናን ቄጤማ የሚያድሉበት ዕለት በመሆኑም ለምለሚቱ ቅዳሜ ትባላለች፡፡ በሐዲስ ኪዳን ጌታ የማዳን ሥራውን ጨርሶ በመቃብር ሲያርፍ በነፍሱ ወደ ሲኦል ወረዶ ሲኦልን ባዶ ያስቀረበት እና የዘላለም ድኅነትን የሰጠበት ዕለት በመሆኑ ቅዱሷ ቅዳሜ ትባላለች፡፡
እሑድ ትንሣኤ ሆኖ የጌታ መነሳት ፋሲካ ሆኖ ይከበራል፡፡

ምንጭ: መጽሐፍ ቅዱስ
ግብረ ህማማት

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleʺበትንሣኤው ቀን እንዳያለቅሱ፣ ወደ ተቸገሩት ገስግሱ”
Next articleቀድሞ በነብያት የተነገረው ሁሉ ይፈፀም ዘንድ ግድ ነበር!