“በአፍሪካ ሕብረት አማካኝነት የሚካሄደው የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርደር እንዲጀመር ኢትዮጵያ ዝግጁ ናት” የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

102

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 13/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ባለፈው ሳምንት በተከናወኑ የዲፕሎሚሲ ሥራዎች እና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥተዋል።
አምባሳደር ዲና በሳምንቱ በፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ እና ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ዙሪያ የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮችን አስመልክተው ነው መግለጫ የሰጡት።
አምባሳደሩ የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአፍሪካ ህብረት የፖለቲካ፣ የሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ ጋር መወያየታቸውን አብራርተዋል፡፡መንግሥት ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት የተለያዩ ርምጃዎችን እየወሰደ እንደሆነ፣ እንዲሁም በአፍሪካ ህብረት አማካኝነት የሚካሄደው የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርደር እንዲጀመር ኢትዮጵያ ዝግጁ መሆኗን ለኮሚሽነሩ ማብራራታቸውን ገልጸዋል፡፡
የእስራኤል የፓርላማ አባላትን እና የሕክምና ባለሙያዎችን ያካተተ የልዑካን ቡድን በጎንደር የሁለት ቀናት ጉብኝት አድርገዋል ፡፡ በጉብኝቱም በሰሜን ኢትዮጵያ በተፈጠረው ግጭት ጉዳት የደረሰባቸውን የጤና ተቋማት መልሶ ለመገንባት የሚደረገውን እንቅስቃሴ ድጋፍ እንዲሰጡ በውይይተ ተነስቷል ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ የዓለም ምግብ ፕሮግራም የአስፈጻሚ ቦርድ አባል ሆና መመረጧንም አብራርተዋል፡፡
በደቡብ አፍሪካ የቱሪዝም ፕሮሞሽን ኤግዚቢሽን እንዲሁም ከዚሁ ጎን ለጎን በተካሄደው የአፍሪካ የቱሪዝም ኢንቨስትመንት ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተሳትፎ በማድረግ፤ ለውጭ ባለሃብቶች ክፍት የሆኑ በቱሪዝም ልማት የተመረጡ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን ማስተዋወቁንም ጠቅሰዋል።
ከሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ካሉ ዜጎች መካከል ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ከ3 ሺህ በላይ ዜጎች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል ብለዋል።
በፈረንሳይ “እኔም ለሀገሬ” በሚል የሚንቀሳቀስ የኢትዮጵያውያን እና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን የመረዳጃ ማኅበር ለተፈናቀሉ ዜጎች አስር ሺህ ዩሮ ድጋፍ ማሰባሰቡን ገልጸዋል።
በሊባኖስ ያለህጋዊ ሰነድ ይኖሩ የነበሩ 32 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፣ በኩዌት ከዲፖርቴሽንና ከሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት በማድረ እና ከ100 በላይ ሰነድ አልባ ዜጎች ወደ ሀገራቸዉ እንዲመለሱ ተደርጓል ነው ያሉት፡፡
በለንደን ኤምባሲያችን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ በተገኙበት ለጥቁር ህዝቦች ታሪክ፣ ቅርስ ማቆያና የትምህርት ማዕከል በአዲስ አበባ እንዲገነባ ያተኮረ ውይይት መደረጉንም ተናግረዋል፡፡
መረጃው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleለበዓል ግብይት ሊውል የነበረ ከ20 ሺህ ብር በላይ ሀሰተኛ የብር ኖት በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡
Next articleበወልቃይት ጠገዴና አካባቢው ሕዝብ ላይ የታቀደ የጅምላ ግድያ ሲፈጽሙ የነበሩ ተፈላጊ ግለሰቦች ዝርዝር ይፋ ሆነ።