ለበዓል ግብይት ሊውል የነበረ ከ20 ሺህ ብር በላይ ሀሰተኛ የብር ኖት በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

138

ፍኖተሰላም: ሚያዝያ 13/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ከተማ አስተዳደር መጪው የትንሣኤ በዓልን ተከትሎ ለግብይት ሊውል የነበረ ሀሰተኛ የብር ኖት በቁጥጥር ስር ማዋሉን የቡሬ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።
በዓላትን ተከትሎ ሀሰተኛ የብር ኖት ዝውውር በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች የሚፈጸም ወንጀል ነው። በቡሬ ከተማ አስተዳደርም ለእንስሳት ግብይትና የሆቴል አገልግሎት ተጠቅሞ ሊከፈል የነበረ በድምሩ ከሁለት ግለሰቦች ከ20 ሺህ ብር በላይ ሀሰተኛ የብር ኖት ከነወንጀል ፈጻሚዎቹ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ መጣራት መጀመሩን የቡሬ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ዋና ኢንስፔክተር መልሰው አበበ ተናግረዋል።
የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በግብይትም ኾነ በመደበኛ እንቅስቃሴ የጸጥታ ችግር እንዳይከሰት በጸጥታ መዋቅሩ እየተሠራ ባለው ሥራ ሀሰተኛ የብር ኖት ዝውውሩ ሊገኝ መቻሉንም ዋና ኢንስፔክተር መልሰው አበበ አስታውቀዋል ።
ከዚህ ባሻገር ከበዓል በፊትና በኋላ ሌሎች ወንጀሎች እንዳይከሰቱ ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል እየተደረገ ነው ያሉት ኀላፊው በተለይ በበዓል ሰሞን የስርቆት፣ የማጭበርበርና ማታለል እንዲሁም ሌሎች ወንጀሎች ሊከሰቱ ስለሚችሉ ኅብረተሰቡ ከጸጥታ ኀይሉ ጋር በመኾን ወንጀለኞችን በማጋለጥና በመከላከል ተባባሪ እንዲኾን ጠይቀዋል።
የምዕራብ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ ኀላፊ ምክትል ኮማንደር በቀለ አብዬ በበኩላቸው መጪው የትንሣኤ በዓል ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበር በዓልን ተከትሎ ሊፈጠሩ የሚችሉ ወንጀሎችን ቀድሞ ለመለየት በሁሉም ወረዳዎች እየተሠራ ነው ብለዋል።
አሁን ላይ ሀሰተኛ የብር ኖት ዝውውር በ3 ወረዳዎች በቁጥጥር ስር መዋሉን ተናግረው የገበያ ላይ ስርቆት፣ ማታለልና ማጭበርበር፣ የእንስሳት ስርቆት እና ሌሎች ወንጀሎችን ለመከላከል በትኩረት እየተሠራ እንደኾነ አስገንዝበዋል።
ዘጋቢ፡-ዘመኑ ይርጋ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleበክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የኢየሱስ ክርሰቶስን ትህትና ለማሰብ የሚከበረዉ ጸሎተ ሐሙስ በአዲስ አበባ በቅድስት ማርያም ገዳም ቤተክርስቲያን እየተከበረ ነው።
Next article“በአፍሪካ ሕብረት አማካኝነት የሚካሄደው የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርደር እንዲጀመር ኢትዮጵያ ዝግጁ ናት” የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር