“የሶስተኛው ምዕራፍ የጤና ተቋማትን መልሶ የመገንባት ተግባር የተደራጀ አቅምና የሁሉንም ርብርብ ይፈልጋል” ጤና ሚኒስቴር

103

አዲስ አበባ: ሚያዝያ 13/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ጤና ሚኒስቴር በጦርነት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን የጤና ተቋማት የመገንባት ተግባሩን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።
መግለጫውን የሰጡት ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር አየለ ተሾመ እንደ ሀገር በተለይም በሰሜን ኢትዮጵያ ባሉ የጤና ተቋማት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል።
ከ80 በላይ ሆስፒታሎች ጉዳት ሲደርስባቸው 40 የሚሆኑት በአማራ ክልል መሆናቸውንም አንስተዋል። ተቋማቱን መልሶ ለመገንባት በተደረገው ጥረትም 26 ሆስፒታሎች ከተቋማት ጋር በተፈጠረላቸው ትስስር ወደ ሥራ እንዲገቡ ተደርጓል ብለዋል።
ሥራ በጀመሩት ሆስፒታሎች አሁንም የላብራቶሪ መሳሪያ ችግር አለብን ያለው ሚኒስቴሩ ረጅ አካላትም በዚህ ላይ ትኩረት እንዲያደርጉልን ስንጠይቅ ቆይተናል፤ አሁን ላይም በመጠኑ እየመጡልን ነው ብሏል።
ከ500 በላይ ጤና ጣቢያዎችም ጉዳት እንደደረሰባቸው ያነሳው ሚኒስቴሩ 467ቱ ወደ ሥራ ገብተዋል፤ ሆኖም አሁንም 40 ጤና ጣቢያዎችና 6 ሆስፒታሎች በፀጥታ ችግር ምክንያት ሥራ እንዳልጀመሩ ተነስቷል።
በደም ባንኮች ላይ የደረሰው ጉዳት ቀላል አለመሆኑንና በተለይ በደሴ ከተማ በደረሰው ጥፋት ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሞብናል ብሏል ሚኒስቴሩ።
በጦርነቱ ወቅት124 አምቡላንሶች በዝርፊያና በውድመት አጥተናል፤ ጉዳት የደረሰባቸውን የመጠገንና 13 አዳዲሲ አንቡላንሶችን የመላክ ሥራ እንደተከናወነም በመግለጫው ተብራርቷል።
ተቋማትን መልሶ የመገንባት ተግባር በሶስት ምዕራፍ ከፍሎ እየሰራ መሆኑንም ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል።
የሶስተኛው ምዕራፍ የጤና ተቋማትን መልሶ የመገንባት ተግባር ትልቅ አቅም የሚጠይቅ በመሆኑ የሁሉንም ርብርብ ይፈልጋል፤ ጊዜ ወሳጅም ነው ብለዋል የጤና ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር አየለ ተሾመ።
ዘጋቢ:–እንዳልካቸው አባቡ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleሕማማቱ ግን የትንሳኤውን ብርሃን አያግዱትም !
Next articleየወረታ ደረቅ ወደብና ተርሚናል ሁለተኛ ዙር ግንባታ በዚህ ዓመት እንደሚጀመር የወደቡ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡