
ባሕር ዳር : ሚያዝያ 11/2014 ዓ.ም (አሚኮ) 50 በመቶ እና በላይ ውጤት አምጥተው ወደ ዩኒቨርስቲዎች መግባት ያልቻሉት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች በክልሉ መምህራን ኮሌጆች በመደበኛው የዲግሪ መርሃ ግብር የመምህርነት ስልጠና እንዲጀምሩ ሰፋ ያለ ቁጥር ለመቀበል ውሳኔ ተላልፎ ዝግጅት እያደረገ መኾኑን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኀላፊ ማተብ ታፈረ (ዶ/ር) አስታውቀዋል።
የ2013 ዓ.ም የ12 ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን ተከትሎ የተፈጠሩ ችግሮችን መፍትሔ ለመስጠት የሚያስችሉ ውሳኔዎች እንዲተላለፉ መደረጋቸውን ኀላፊው ገልፀዋል።
እስካሁንም በተላለፉ ውሳኔዎችም ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀን እንዲራዘም ተደርጓል።
ወደ ዩኒቨርስቲ መግቢያ ነጥብ ያላመጡት ሁሉም የክልሉ ተማሪዎች በመደመበኛ ተማሪነት ፈተናውን በድጋሜ እንዲወስዱ ተወስኗል።
ተጨማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ የተወሰነላቸው 4 ሺህ 339 ተማሪዎች ደግሞ 50 በመቶ እና ከዛ በላይ ካመጡ ከክልሉ ሁሉም ዞኖች መካከል ተማሪዎች በውጤታቸው ቅደም ተከተል የሚመረጡ ይኾናል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሌሎች 50 በመቶ እና በላይ ውጤት አምጥተው ወደ ዩኒቨርስቲዎች መግባት ያልቻሉት ደግሞ በክልሉ መምህራን ኮሌጆቾ በመደበኛው የዲግሪ መርሃ ግብር የመምህርነት ስልጠና እንዲጀምሩ ሰፋ ያለ ቁጥር ለመቀበል ዝግጅት እየተደረገ መኾኑን ዶ/ር ማተብ አብራርተዋል።
በዚህ ሁሉ ጥረት ውስጥ ወደ ዩኒቨርስቲዎችም ሆነ ወደ መምህራን ኮሌጆች መግባት ያልቻሉት ተማሪዎች ደግሞ በቂ ዝግጅት አድርገው መፈተን እንዲችሉ የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የፈተና ጊዜ እንዲራዘም ለትምህርት ሚኒስቴር ቢሮው ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ከመስከረም 2015 ዓ.ም በፊት ፈተናው እንደማይሰጥ ተወስኗል ብለዋል ኀላፊው።
የ2014 ዓም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከመስከረም 20 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ጊዜያት ሊሰጥ እንደሚችል ተፈታኞች አውቀው ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ኀላፊው አሳስበዋል። በክልሉ ትምህርት ቢሮ ማኀበራዊ ትስስር ገጽ ይፋ በተደረገው መረጃ ለተፈታኝ ተማሪዎች በቢሮው በኩል አስፈላጊው ሁሉ ድጋፍ የሚደረግ መኾኑንም ዶ/ር ማተብ አረጋግጠዋል ።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/