የአምነስቲና የሂዩማንራይትስዎች ጥምር የምርመራ ሪፖርት አድሏዊና ችግር ያለበት መኾኑን አብን ገለጸ።

100

ሚያዝያ 11/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አምነስቲ ኢንተርናሽናልና ሂዩማን ራይትስዎች ያወጡት ጥምር የምርመራ ሪፖርት የመረጃ አሰባሰብ፣ የመረጃ ትንተና፣ ድምዳሜውና በመፍትሔነት ያስቀመጡት ሐሳብ አድሏዊና ችግር ያለበት መኾኑን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ገለጸ፡፡
የአብን ምክትል ሊቀመንበር አቶ መልካሙ ሹምዬ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ ተቋማቱ ያወጡት ሪፖርት ዓለም አቀፍ የምርመራ ደረጃን አያሟላም፤ አድሏዊና ችግር ያለበትም ነው።
የተዛባና የአንድ ወገን ፍላጎትን ለማሳካት የተሠራ፣ ሕወሓት በኀይልና በጠመንጃ አፈሙዝ ሞክሮ ያላሳካውን በዲፕሎማሲና ዓለምአቀፍ ጫና ፈጥሮ ለማሳካት ታቅዶ የተተገበረ ፖለቲካዊ ዓላማን ለማሳካት የተሠራ ሪፖርት መኾኑንም አመልክተዋል፡፡
በተለይም በሰብዓዊ መብት ላይ ወንጀል ተፈጽሟል ከተባለ ተፈጸመ የተባለው ወንጀል ከምክንያታዊ ጥርጣሬ በላይ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡ ወንጀል የፈጸሙ ሰዎችን በስልክ በማነጋገር ተሠርቷል ያሉትም ቢኾን ተገቢውን የመረጃ አሰባሰብ ደረጃን አያሟላም ብለዋል፡፡
የተቋማቱ ሪፖርት ተጠቂውን አጥቂ በተቃራኒው ደግሞ አጥቂውን ተጠቂ አድርጎ ያስቀመጠ በመኾኑ ተቀባይነት የለውም ያሉት አቶ መልካሙ ሪፖርቱ በአማራ በኩል ያለውን መፈናቀልና ግድያ አለማንሳቱ አድሏዊነቱን በግልጽ እንደሚያሳይም ገልጸዋል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየመንግሥት ሥራዎችን በዲጂታል ለማከናወን የሚያስችሉ የሥራ ትስስር ማዕከላት በ6 ተቋማት ተግባራዊ ሊደረግ ነው፡፡
Next articleበ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና 50 በመቶ እና በላይ ውጤት አምጥተው ወደ ዩኒቨርስቲዎች መግባት ያልቻሉ ተማሪዎች በክልሉ መምህራን ኮሌጆች እንዲሠለጥኑ ተጨማሪ ውሳኔ ተላለፈ።