
ሚያዝያ 11/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የሥራ ትስስር ማዕከላቱ የመንግሥት ሥራዎች በግንኙነቶች ሳይቆራረጡ፣ ጊዜና ቦታ ሳያግዳቸው በዲጂታል መልኩ እንዲሠሩ የሚያደርግ አሠራር የሚተገበርባቸው ናቸው፡፡
በመጀመሪያው ምዕራፍ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ በገንዘብ ሚኒስቴር፣ በትምህርት ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ ኮምዩኒኬሽን ባለስልጣን እና በብሔራዊ መታወቂያ ፕሮጄክት ውስጥ ተግባራዊ የሚደረጉ ናቸው፡፡
ፕሮጀክቱን በጨረታ ያሸነፈው አይ ኢ ኔትወርክ ሶሉሽን የሚያከናውነው ሲኾን በ120 ቀናት ውስጥ አጠናቅቆ ለማስረከብ ስምምነት አድርጓል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ እንዳሉት የዲጂታል 2025 ስትራቴጂ ያለግሉ ዘርፉ ተሳትፎ እውን አይኾንም። በኹሉም የልማት ሥራዎች የግል ዘርፉ አጋር ብቻ ሳይኾን ባለቤትም እንዲኾን እየሠራን ነው ብለዋል፡፡
በዲጂታል ፋውንዴሽን ፕሮጀከት ሥር በመተግበር ላይ ካሉት ሥራዎች ውስጥ የመንግሥት የሥራ ትስስር ማዕከል ልማት አንዱ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ ሥርዐቱ የመንግሥት ተቋማት ሥራዎች ጊዜና ቦታ ሳይገድባቸው የሚከወኑበት መኾኑን ተናግረዋል፡፡
በኹለተኛው ምዕራፍ ትግበራ በ50 የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እና ክልሎች ጭምር ተግባራዊ እንደሚደረግ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/