
ሚያዝያ 11/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ወረታ ወደብና ተርሚናል በሰሜን-ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ አስመጭና ላኪዎች የተቀላጠፈ የደረቅ ወደብ አገልግሎት እንዲያገኙ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።
የወደቡ ተጠቃሚዎች እንደገለጹት ከጅቡቲ – ሞጆ – በአዲስ አበባ ወደ ባሕር ዳርና ሌሎች የሰሜን-ምዕራብ አካባቢዎች የሚጓጓዙ ቁሳቁስ አቋራጭ በኾነ መንገድ ከጅቡቲ -ሚሌ -ኮምቦልቻ -ወረታ ለማስገባት አስችሏል። ይደርስ የነበረውንም የጊዜና የገንዘብ ብክነት ቀንሷል።
የወረታ ወደብና ተርሚናል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሥራ አስኪያጅ ተስፋየ አያሌው ወደቡ ብዛት ያላቸው ኮንቴነሮችን አስተናግዷል ብለዋል። በ2014 ዓ.ም የበጀት ዓመት ግን በአሸባሪው ቡድን ወረራ ምክንያት መንድ በመዘጋቱ 1 ሺህ 520 ኮንቴነሮችን ብቻ እንዳስተናገዱ ነግረውናል።
“መተላለፊያ መንገዱ ከወረራ ነጻ ከወጣ በኋላም በሽብር ብድኑ የፈረሰው የጨረቲ ወንዝ ድልድይ ባለመጠገኑ የምንቀበላቸው ኮንቴነሮች ከጅቡቲ በአዲስ አበባ አድርገው ወረታ የሚመጡ ነበሩ” ብለዋል። ይህም በወጭ ደረጃ ሲታይ አንድ ትልቅ ኮንቴነር ከጅቡቲ -ሚሌ – ጭፍራ- ወልዲያ – ወረታ ሲመጣ እስከ 60 ሺህ ብር ወጭ ሲኖረው ከጅቡቲ በአዲስ አበባ ወረታ ሲገባ ግን እስከ 200 ሺህ ብር ወጭ እንዳለው ሥራ አስኪያጁ አስረድተዋል።
የወደቡ ሥራ አስኪያጅ በቅርብ የተጠገነው የጨረቲ ወንዝ ድልድይ ለአገልግሎት ክፍት በመኾኑ ኮንቴነሮች በሚሌ – ጭፍራ- ወልዲያ – ወረታ መምጣት ጀምረዋል ብለዋል። ይህ መኾኑ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት እቃዎችን ለማስገባት ይደርስ የነበረውን የጊዜና የገንዘብ ወጭ ዳግም ቀንሷል። ይሁን እንጅ የወደቡ ደንበኞች ገና ሙሉ በሙሉ አለመመለሳቸውን አቶ ተስፋየ ተናግረዋል።
አሁን ላይ መንገዱ ክፍት መኾኑ ታውቆ አስመጭና ላኪዎች ወረታ ወደብና ተርሚናልን በመጠቀም የተለመደ ንግድና ኢንቨስትመንታቸውን ማስቀጠል እንደሚችሉም ነው የገለጹት።
“በተለመደው የሚሌ – ጭፍራ- ወልዲያ – ወረታ መስመር ኮንቴነሮችን መቀበል በመጀመሩ ደንበኞች በዚሁ መንገድ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲኾኑ ሥራ አስኪያጁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ፡- አሚናዳብ አራጋው
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/