
ሚያዝያ 10/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ‘ኤችአር 6600’ እና ‘ኤስ 3199’ ረቂቅ ሕጎችን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ተካሄደ።
ኋይት ሐውስ ፊት ለፊት በተካሄደው ሰልፍ “ማዕቀብ ይገድላል” ፣ “ጸረ-ኢትዮጵያ፣ ኤርትራና አሜሪካ የኾኑትን ረቂቅ ሕጎች እንቃወማለን”፣ ‘ ኤችአር 6600’ እና ‘ኤስ 3199’ ይሰረዙ” እና ”ፍላጎትን በኀይል ለመጫን የሚደረግ ማንኛውም ድርጊት እንቃወማለን አንቀበልም” የሚሉ መልዕክቶች መተላለፋቸውን ኢዜአ ከሰላምና አንድነት ለኢትዮጵያ ማኅበር የዋሽንግተን ግብረ ኀይል ያገኘው መረጃ ያመላክታል።
ረቂቅ ሕጎቹ ኢትዮጵያን እንዲሁም የኢትዮጵያና አሜሪካን የረጅም ጊዜ ግንኙነት የሚጎዱ በመኾናቸው በፍጥነት መሰረዝ አለባቸው የሚሉ መፈክሮች በሰልፉ ላይ መሰማቱን ተገልጿል።
ሕጎቹ በኢትዮጵያ ሰላምን ለማምጣት እየተደረገ ያለውን ጥረት እውቅና ያልሰጠና የሰላም ሂደቱን አሉታዊ ተጽእኖ የሚያሳድር ነው ብለዋል ሰልፈኞቹ።
‘ኤችአር 6600’ እና ‘ኤስ 3199’ ረቂቅ ሕጎችን በመቃወም በኋይት ሐውስ ፊት ለፊት የሚካሄደው ሰልፍ በቋሚነት በየሳምንቱ እንደሚከናወን የሰላምና አንድነት ለኢትዮጵያ ማኅበር የዋሺንግተን ግብረ ኀይል አስታውቋል።
በተያዘዘ ዜና ‘ኤችአር 6600’ እና ‘ኤስ.3199’ ረቂቅ ሕጎችን የሚቃወም ሰልፍ ከነገ በስቲያ በኒው ጀርዚ ግዛት ይካሄዳል።
ሰልፉ የ‘ኤስ.3199’ ረቂቅ ሕግ አርቃቂ ሴናተር ሮበርት ሜኔንዴዝ (ኒው ጀርዚ) ቢሮ ፊት ለፊት እንደሚካሄድ ተገልጿል።
በአሜሪካ የኮንግረስ አባል ቶም ማሊኖውስኪ (ኒውጀርሲ) ዋና አርቃቂነት፣ በያንግ ኪም (ካሊፎርኒያ)፣ ግሪጎሪ ሚክስ (ኒው ዮርክ)፣ ዴቪድ ሲሲሊን (ሮድ አይላንድስ)፣ ብራድ ሼርማን (ካሊፎርኒያ) እና ማይክል ማካውል (ቴክሳስ) ደጋፊነት የተዘጋጀው ‘ኢትዮጵያ ስታብላይዜሽን ፒስ ኤንድ ዴሞክራሲ አክት’ ወይም ኤችአር 6600 ረቂቅ ሕግ የኮንግረሱ የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ተወያይቶበት ለኮንግረሱ መምራቱ የሚታወስ ነው።
የ‘ኤች አር 6600’ ተጓዳኝ ወይም አጋዥ (ኮምፓኒየን ቢል) የኾነው የኢትዮጵያ ፒስ ኤንድ ዴሞክራሲ ፕሮሞሽን አክት ኦፍ 2022’ ወይም ‘ኤስ.3199’ በአሜሪካ ሴናተር ሮበርት ሜኔንዴዝ (ኒው ጀርዚ) ዋና አርቃቂነት፣ በሴናተር ጀምስ ሪስች (ኢዳሆ)፣ በሴናተር ክሪስ ኩንስ (ዴልዌር) እና በሴናተር ቶም ቲሊስ (ኖርዝ ካሮላይና) ደጋፊነት የተዘጋጀ ሲኾን፤ ሴኔቱ እ.አ.አ በ2022 ሊመለከታቸው በጊዜ ሰሌዳው ከያዛቸው ረቂቅ ሕጎች አንዱ ኾኖ እንዲካተት መወሰኑ ይታወሳል።
በአሜሪካ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ረቂቅ ሕጎቹ በሕግ አውጪው አካል ድምጽ ተሰጥቶባቸው እንዳይጸድቁ ለማድረግ ሴናተሮችና የኮንግረስ አባላትን በማናገር፣ ደብዳቤ በመጻፍ፣ ሰላማዊ ሰልፍ በማካሄድ፣ፊርማ በማሰባሰብና በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ዘመቻ በማድረግ ጥረት እያደረጉ ነው።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/