በፀጥታና ደኅንነት ጉዳዮች ዙርያ ሲመከሩ የቆዩት የምሥራቅ አፍሪካ ወታደራዊ መረጃ ተቋማት በጋራ ለመሥራት ተስማሙ።

343

ሚያዝያ 09/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የምሥራቅ አፍሪካ ወታደራዊ መረጃ ተቋማት”ሰላማዊ እና ደኅንነቷ የተረጋገጠ አፍሪካን ” ለመፍጠር በድንበር፣ በሳይበር፣ በማኅበራዊ ሚዲያ ዙርያ፣ በማኅበራዊ ጉዳዮች፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በወጣቶችና ሥራ አጥነትን ለመቅረፍና በሌሎችም ጉዳዮች ለመሥራት ተስማምተዋል።

አሸባሪዎችንና ፀረ ሰላም ኀይሎችን በጋራ ለመከላከል የሚያስችል ሰነድም ተፈራርመዋል።

የምክክር መድረኩ ከደኅንነት ጉዳዮች ባለፈ በዘርፉ የልምድ ልውውጥን ያካተተ ሲኾን የመከላከያ ዋና መሥሪያ ቤትን፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነትን እና የኢትዮጵያ አርተፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲትዩት መሥሪያ ቤቶችን ጎብኝተዋል።

በምክክር መድረኩ የተሳተፉ ሀገራት ኢትዮጵያ፣ ጁቡቲ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን፣ ታንዛኒያ እና ዩጋንዳ ናቸው። ተሳታፊ ሀገራት ኢትዮጵያ ለፎረሙ መሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረጓ ምሥጋና አቅርበዋል።

ቀጣዩን የምክክር መድረክ ዩጋንዳ እንደምታዘጋጅ መገለጹን ከመከላከያ ሠራዊት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“ምዕመናን በሰሙነ ሕማማት ክርስቲያናዊ ተግባራትን መፈጸም አለባቸው” ብፁዕ አቡነ አብርሃም
Next article“ዩሪያ የአፈር ማዳበሪያ ከቀጣይ ሣምንት ጀምሮ ወደ አገር ውስጥ ይገባል” ግብርና ሚኒስቴር