“ምዕመናን በሰሙነ ሕማማት ክርስቲያናዊ ተግባራትን መፈጸም አለባቸው” ብፁዕ አቡነ አብርሃም

582

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 09/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሰሙነ ሕማማትን ምክንያት በማድረግ ለክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች መልእክት አስተላልፏል።

መልእክቱን ያስተላለፉት የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ የሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ አብርሃም የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች በሰሙነ ሕማማት የተራቡና የተጠሙ ወገኖችን ሊደግፉ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ምዕመናን በተለይ በሰሙነ ሕማማት ክርስቲያናዊ ተግባራትን መፈጸም እንዳለባቸው መክረዋል።

“መጾምና መጸለይ ዋጋ የሚያስገኘው የተቸገሩትን ሲረዱና ሲደግፉ ነው” ብለዋል። በርካታ ወገኖች ከነበሩበት ሕይወት ወጥተው በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ስለሚገኙ በዓሉ ሲከበርም የምግብ፣ አልባሳት እና ሌሎችንም ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ ነው ያሳሰቡት።

“ከቤተክርስቲያን የተማርነውን ተግባራዊ ማድረግ አለብን” ነው ያሉት ብፁዕነታቸው።

ምዕመናን በጾምና በጸሎት ወቅት ለተቸገሩ ሰዎች ድጋፍ ማድረግ በተጨማሪ ይቅር መባባል እንዳለባቸውም መክረዋል።

በተለይ በአሁኑ ወቅት ጭፈራና ደስታ ማድረግ ሳይኾን የመደጋገፍ፣ የመጾምና የመጸለይ ወቅት ነው ብለዋል።

ብፁዕነታቸው እንዳሉት ምዕመናን በሰሙነ ሕማማት በይበልጥ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያቀራርብ ተግባራትን መፈጸም አለባቸው።

ሀገረ ስብከቱ ዘመን አሻጋሪ የተባለ ግብረኃይል በማቋቋም ለተፈናቃዮች ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ገልጸዋል። ችግሩ እስኪቀረፍ ድረስ ሀገረ ስብከቱ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው ብፁዕነታቸው የተናገሩት።

ምዕመናን በባሕር ዳር ከተማ የሰላም አርጊው ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ለተቃጠለው የአብነት ተማሪዎች መኖሪያ የሚውል የመልሶ ግንባታ ድጋፍ እንዲያደርጉም ጠይቀዋል።

ምዕመናን ለአብነት ተማሪዎች ሲባል ሀገረ ስብከቱ በከፈተው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር 0307 ወይም 1000469844289 ገቢ በማድረግ ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚገባም ብፁዕነታቸው ጥሪ አድርገዋል።

ዘጋቢ:- ቡሩክ ተሾመ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

Previous article“የውስጥ ማንነትን የሚያስፋ እና ራስን ማዳመጥ የሚያስችሉ የሥነ ጽሑፍ ውጤቶች ለትውልዱ ያስፈልገዋል” ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ
Next articleበፀጥታና ደኅንነት ጉዳዮች ዙርያ ሲመከሩ የቆዩት የምሥራቅ አፍሪካ ወታደራዊ መረጃ ተቋማት በጋራ ለመሥራት ተስማሙ።