
ሚያዝያ 09/2014 ዓ.ም (አሚኮ)የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሠራተኞች የዘጠኝ ወራት የእቅድ አፈጻጸምና በመንግሥት ሠራተኞች የድልድል መመሪያ ላይ ተወያይተዋል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ.ር) ባለፉት ወራት የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ፣ ምቹ የኢኖቬሽን ሥነ ምህዳር መፍጠር፣ የመንግሥት የኤሌክትሮኒክስ አገልግሎት መሠረተ ልማት ዝርጋታ ላይ አበረታች ሥራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል።
የተቀናጀ የኢንተርፕራይዝ ሃብትን የማስተዳደሪያ ሥርዐት በኹሉም የፌዴራል ተቋማት አገልግሎት ላይ ለማዋል የታየው ጅምር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለጻቸውን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
የኤሌክትሮኒክ ቢሮ አሠራር ላይ ተቋሙ ግንባር ቀደም ኾኖ በኹሉም የመንግሥት ተቋማት ለማስተገበር እየሠራ ስለመኾኑ ያብራሩት ሚኒስትሩ ለስኬቱ ሠራተኞች በቅንጅት እንዲሠሩ አሳስበዋል።
በውይይቱ በትግበራ ሂደት ላይ የሚገኙትን የዳታ ማዕከል ግንባታ፣ የኤሌክትሮኒክ መሠረተ ልማት ማሻሻል፣ የመንግሥት ፖርታሎችን ማልማትና ማሻሻል ትኩረት የሚፈልጉ ጉዳዮች መኾናቸው ተነስቷል።
የአስር ዓመቱን እቅድ ለማሳካት ያለመው አዲሱ የሠራተኛ ድልድል መመሪያ ላይ ውይይት ተደርጓል።
በተቋሙ ለዓመታት ያልተቋጩ ሥራዎችን ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መኾኑን የገለጹት ሚኒስትሩ ለስኬቱ ሠራተኛው በትብብር መንፈስ እንዲሠራም አሳስበዋል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/