ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የተሳካ ሮኬት አስወነጨፈ።

1918

ደብረ ታቦር: ሚያዝያ 08/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ከሦስተኛው ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደበው የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የአፄ ቴዎድሮስን የዕውቀት ጥያቄ የመመለስ ራዕይ አንግቦ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው የአፄ ቴዎድሮስን 154ኛ ዝክረ ሰማእት ምክንያት በማድረግ አሞራ ገደል በተባለ ሥፍራ የተሳካ የሮኬት ማስወንጨፍ
ሙከራ አካሂዷል።

ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ያደረገው ሙከራ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን ባለፉት ዓመታት የተለያዩ የቴክኖሎጅ ምርምሮችን ሲያካሂድ መቆየቱን የዩኒቨርሰቲው ፕሬዚደንት ዶክተር አነጋግረኝ ጋሻው ተናግረዋል።

ይህ ምርምር አድጎ ለሀገሪቷ የሕዋ ሳይንስ ምርምር አጋዥ እንዲሆን ተግባሩ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ሌላው በዝክረ ሰማእት መታሰቢያ ዕለቱ የአፄ ቴዎድሮስን የመድፍ ሥራ የሚያስታውስ ምስለ ሴባስቶፖል መድፍ ተሰርቶ በደብረ ታቦር ከተማ የመተኮስ ሥነ ሥርዓት ተከናውኗል።

ዘጋቢ:-አወቀ ካሴ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“የሥራ እኩልነት መርሃቸው ነው። ሠርቶ መለወጥን በተግባር ያሳያሉ” አውራምባዎች
Next article“ኑ የፍቅር ካባ እናልብሳችሁ፣ ከደግነት ምንጭ እናጠጣችሁ”