በቀጣዩ ሃገር አቀፍ ምርጫ ላይ የሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሴቶች ተሳትፎ ትኩረት እንዲሰጡ ተጠየቀ፡፡

162

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባዔ ወይዘሮ ሽታዬ ምናለ የፊንላንድ ፓርላማ ልዑካን ቡድን እና መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት አባላትን ዛሬ በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አወያይተዋል፡፡

በውይይቱም ፊንላንድ በኢትዮጵያ ለሚካሄደው ለውጥ ሙሉ ድጋፏን እንደምትሰጥ ተገልጿል፡፡ የለውጥ ሂደቱ ከዚህ በበለጠ ሁሉን አቀፍ እንዲሆን ሊሰራበት እንደሚገባም ሀሳብ ሰጥተዋል፡፡

ምክትል አፈ-ጉባዔ ወሮ. ሽታዬ ምናለ በበኩላቸው በቀጣዩ ሀገር አቀፍ ምርጫ ላይ የሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሴቶች ተሳትፎ በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

ለዚህም አሁን ከፊንላንድ የመጡት እና ሌሎች መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ድጋፍ ከማድረግ ባለፈ ተፅዕኖ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡

ምንጭ፦ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

Previous articleባለቤት ያጣው የረጅም ርቀት መንገደኞች የአካባቢ ብክለት እና መፍትሔው!
Next articleበቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የተገነባው የሎዛ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለምረቃ ዝግጁ ሆኗል።