
ጎንደር: ሚያዝያ 08/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በከፈተው ጦርነት ምክንያት ትግራይ ክልል መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን አቋርጠው የነበሩ 85 የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የማርኬቲንግ ማኔጅመንት ተማሪዎች በጎንደር ዩንቨርሲቲ ተመድበው ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተው ዛሬ ተመርቀዋል።
ተማሪ ሜላት ጌታቸው ለአሚኮ እንዳለችው በወቅቱ በተፈጠረው ጦርነት ትምህርቷን አቋርጣ ከባድ ችግር ውስጥ እንደነበረች አስታውሳለች፡፡ እሷና ጓደኞቿ በመኖርና አለመኖር ውስጥ ኾነው መጥፎ ጊዜ ማሳለፋቸውንም ገልጻለች።
ሌላኛው ተማሪ ህላዌ ለጥአርጋቸው የተካሄደው ጦርነት እና ሀገር የማጥፋት ሥራ በትምህርታቸው ላይ ብዙ ጫና እንደፈጠረባቸው ነው ያስረዳው።
ተማሪዎቹ ካሳለፉት ፈተና በኃላ በጎንደር ዩንቨርሲቲ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተው በመመረቃቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል። ያሳለፉት ችግርም በቀጣይ ለፈተናዎች ዝግጁ እንዲኾኑ እንደሚያግዛቸው ነው የተናገሩት።
የጎንደር ዩንቨርሲቲ የአካዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንትና የፕሬዚዳንት ተወካይ ካሳሁን ተገኘ (ዶ.ር) ለተመራቂ ተማሪዎቹ የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል።
ዶክተር ካሳሁን አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በከፈተው ወረራ ምክንያት በትግራይ ክልል ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን አቋርጠው የነበሩ 740 ተማሪዎች በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ መመደባቸውን ተናግረዋል፡፡
ፈተና ያበረታልና ብዙ ፈተናዎች ቢያጋጥማችሁም ችግሮችን አልፋችሁ ለዚህ በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
ዶክተር ካሳሁን ተመራቂዎችን የሰላም እጦት ምን ያክል አስቸጋሪ እንደኾነ በተግባር የተረዳችሁ በመኾናችሁ በሄዳችሁበት ሁሉ የሰላም አምባሳደር እንድትኾኑ ሲሉ አሳስበዋል።
የተማሪ ወላጆች በበኩላቸው ልጆቻቸው መቀሌ ዩኒቨርሲቲ በነበሩበት ጊዜ ለአንድ ወራት ያክል ሳይገናኙ መቆየታቸው ጭንቀት ፈጥሮባቸው እንደነበር ገልጸው አሁን ላይ ሁለተኛ እንደተወለዱ እንደተሰማቸው ተናግረዋል።
ወላጆቹ የጎንደር ዩኒቨርሲቲና የአካባቢው ማኅበረሰብ ልጆቻቸው እስኪመረቁ ላደረገው አስተዋጽኦ ያላቸው አክብሮት ላቅ ያለ መኾኑን ነው የተናገሩት።
ዘጋቢ፡- ደስታ ካሳ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/