ምሁራን የሐሰት ትርክቶችን በማረምና ሀገር በቀል የግጭት አፈታት ዘዴዎችን በማጎልበት ሀገራዊ የምክክር መድረኩ ውጤታማ እንዲሆን መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተገለጸ።

146

ደብረብርሃን: ሚያዝያ 08/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር አካታች ብሔራዊ ምክክርን ለማሳካት የምሁራኑ ሚና ምን መሆን አለበት በሚል መሪ ሀሳብ ውይይት ተደርጓል።

የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት እና የፕሬዚዳንቱ ተወካይ ዶክተር ደረጄ አንዳርጌ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን ያላቸውን እውቀት እና ክህሎት ሀገራዊ ሰላምን በሚያረጋግጥ መልኩ መጠቀም ይገባቸዋል ብለዋል።

የጋራ የሆነ እውነትን በመያዝ የሀሰት ትርክትን በማረም እና ሀገር በቀል የግጭት አፈታት ዘዴዎችን በማጎልበት ብሔራዊ የምክክር መድረኩ ውጤታማ እንዲሆን ምሁራኑ መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

ሌሎች የምክክር መድረክን የተጠቀሙ የዓለም ሀገራትን ተሞክሮ በማጥናት ጠንካራ ጎኖችን በመጠቀም ችግሮችን በማጤን ወደ ችግር እንዳይገባ መንገዶችን ማስቀመጥ ከምሁራኑ የሚጠበቅ ነው ያሉት ደግሞ በሰላም ሚኒስቴር በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የሚኒስተሩ አማካሪ ካይዳኪ ገዛኸኝ ናቸው።
ከስሜታዊነት መፅዳት፣ ምክንያታዊነት እና መደማመጥ ከሁሉም የሚጠበቅ እንደሆነም ተናግረዋል።

አካታች ብሔራዊ ምክክር ከማሳካት አንፃር የምሁራኑ ሚና በሚል ርእስ ጥናታዊ ጹሑፍ በኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው ቀሮቦ ከወሎ ዩኒቨርሲቲ፣ መቅደላአምባ፣ ወልዲያ እና ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ከመጡ መምህራን ጋር ውይይት ተደርጎበታል።

ዘጋቢ:-ገንዘብ ታደሰ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“የዉጭ ወራሪዎች ኢትዮጵያን ለመዉረር በተነሱበት ወቅት የሀገራችን ዳር ድንበር ለማስከበር የታገልን የቁርጥ ቀን ልጆች ነን ” ብርጋዴል ጀነራል ዉበቱ ጸጋየ
Next articleየአውራምባ ማኅበረሰብን መልካም እሴቶች በማስፋት እንደ ሀገር ለሚታየው ቀውስ መውጫ መንገድ መጠቀም እንደሚገባ ተገለጸ።