“የዉጭ ወራሪዎች ኢትዮጵያን ለመዉረር በተነሱበት ወቅት የሀገራችን ዳር ድንበር ለማስከበር የታገልን የቁርጥ ቀን ልጆች ነን ” ብርጋዴል ጀነራል ዉበቱ ጸጋየ

162

አዲስ አበባ: ሚያዚያ 08/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የቀድሞ የኢትዮጵያ ሠራዊት የድጋፍ የልማት ማኅበር ጠቅላላ ጉባኤዉን እያካሄደ ነው። በጉባኤው አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ወረራ በፈጸመበት ወቅት በጦር ግንባር ለተሳተፉ ጀግኖችም እዉቅና እየተሰጠ ነው።

በመድረኩ የተገኙት ብርጋዴል ጀነራል ዉበቱ ጸጋየ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የቀድሞ ሠራዊቱ እንዲጠላ ሰርቷል ብለዋል።

የቀድሞው ጦር ተፈላጊነት ሁሌም እየጨረ ይሄዳል ያሉት ብርጋዴል ጀነራሉ ጀግናዉ የቀድሞ ጦር ሁሌም በሙሉ ጀግንነት ታሪክን ሲፈጽም ቆይቷል ነው ያሉት።

ለዚህ ጀግና ሠራዊት ቀደም ሲል በስልጣን ላይ በነበረዉ መንግሥት የተሰጠዉ ክብር አግባብነት ያልነበረዉ እና ጀግኖችን የከዳ ነበር ብለዋል።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ሠራዊት የድጋፍ እና የልማት ማኅበር ፕሬዚዳንት ሃምሳ አለቃ ብርሃኑ አማረ ‟ሀገር ስትነካ የሚያመን፤ የሀገር ቁስል ቁስላችን የኾንን ወታደሮች ነን፤ ለሀገራችን አሁንም ዘብ እንቆማለን” ብለዋል፡፡

ሃምሳ አለቃ ብርሃኑ ተጥሎ የነበረውን የቀድሞ የኢትዮጵያ ሠራዊት እንደ አዲስ በማደራጀት ኢትዮጵያዊነት እንዲለመልም ተደርጓል ሲሉ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያዊነት ያገናኛቸዉ የቀድሞ ሠራዊት አባላት ለሀገራቸዉ ዋጋ ለመክፈል የተዘጋጁ መኾናቸዉንም የልማት ማኅበሩ ፕሬዚዳንት አስገንዝበዋል።

ማኅበሩ በ2012 ዓ.ም ከተቋቋመ በኋላ በየክልሎቹ አባላትን በማፍራት ጠንካራ ተቋማዊ አደረጃጀት መመስረት ተችሏልም ነው ያሉት።

የቀድሞ ሠራዊት በርካታ አባላትን ከማፍራቱም ባለፈ ኢትዮጵያ በምትፈልገው ጊዜ ሁሉ ዝግጁ ኾኖ በመገኘት ታሪክ የሠራ የጀግኖች ስብስብ ነው ሲሉም ገልጸዋል።

የቀድሞ የሠራዊት አባላቱ ሀገር ከጎኔ ሁኑ ባለችበት ወቅት ወራሪዉን ቡድን ለመደምሰስ ከባድ ተጋድሎ አድርገዋል ለዚህም ክብር ይገባቸዋል ብለዋል።

የቀድሞ ሠራዊት አባላት ልማት ማኅበር ብዙዎች ለሞቱላት ሀገር ለመሞት ዝግጁ የኾነ ሠራዊት ያለበት እንደኾነም አስገንዝበዋል።

ማኅበሩ በጠቅላላ ጉባኤዉ ለቀድሞ ሠራዊት አባላት ትኩረት ሊሰጠዉ እንደሚገባም ተነስቷል።

በመድረኩ የተገኙት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ኢትዮጵያ በነፃነት እንድትኖር ግንባር ቀደም የኾናችሁ እናንተ የቀድሞ ሠራዊት አባላት ናችሁ ብለዋል፡፡

አምባሳደር ዲና ኢትዮጵያ ለሌሎች ነፃነት ተምሳሌት እንድትኾን በኮንጎ እና በላይቤሪያ በመሳተፍ ታሪክ ማስመዝገባቸውንም አስረድተዋል፡፡

ለዲፕሎማሲውም መሰረት ናችሁ ነው ያሉት። ኢትዮጵያ ከሌሎች ሀገራት ጋር ላላት መልካም ግንኙነት ግንባር ቀደም ድርሻዉን የሚወስዱት የቀድሞው ሠራዊት አባላት ናቸው ብለዋል፡፡

አምባሳደር ዲና ‟አሁንም ሀገር በምትፈልጋችሁ መስክ ሁሉ ሀገርን እንደምታኮሩ ተስፋ አደርጋለሁ” ሲሉ መልእክታቸዉን አስተላልፈዋል፡፡

ዘጋቢ፡-ኤልሳ ጉዕሽ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየምሥራቅ አፍሪካ የመከላከያ ደኅንነት ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
Next articleምሁራን የሐሰት ትርክቶችን በማረምና ሀገር በቀል የግጭት አፈታት ዘዴዎችን በማጎልበት ሀገራዊ የምክክር መድረኩ ውጤታማ እንዲሆን መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተገለጸ።