የምሥራቅ አፍሪካ የመከላከያ ደኅንነት ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

140

አዲስ አበባ: ሚያዚያ 08/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የምሥራቅ አፍሪካ የመከላከያ ደኅንነት ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። ለ3 ቀናት በሚቆየው ፎረም የ7 ሀገራት ተወካዮች የሚሳተፉ ሲኾን በቀጣናው የሚንቀሳቀሱ አሸባሪ ቡድኖችን በመከላከል የሕገውጥ የሰዎች ዝውውር አንዲሁም የአደንዛዥ እፅ ዝውውርን በጋራ በመከላከል ዙሪያ ይመክራል ተብሏል።

ፎረሙን በንግግር የከፈቱት የኢፌዴሪ የመከላከያ መረጃ ዋና መምሪያ ኀላፊ ሌቴናንት ጀኔራል ብርሃኑ በቀለ ይህ የጋራ የመከላከያ ኀይል በቀጠናው የሚንቀሳቀሱ ዓለም አቀፍ እና በሀገር ውስጥ ያሉ አሸባሪዎችን መከላከል ላይ ቅድሚያ ሰጥቶ ሊሠራ ይገባል ብለዋል።

አንደ አልሸባብ እና አይ ኤስ አይ ኤስ ያሉ ዓለም አቀፍ የሽብር ቡድኖችን ጨምሮ እንደ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን እና እንደ አሸባሪው ሸኔ ያሉ በየሀገራቱ የሚገኙ አሸባሪዎችን በጋራ በመከላከል ወደ ሕገወጥ የመሳሪያ እና የሰዎች ዝውውር መከላከል መሸጋገር ያስፈልጋል ብለዋል።

የአንዱ ችግር ለሌላውም የሚተርፍ በመኾኑ ለሕዝቦች ሰላም እና አንድነት መሥራት እንደሚገባ ነው አጽኖት ሰጥተው የተናገሩት።

የመከላከያ ደኅንነት ትልቁ ሥራው የፖሊሲ አቅጣጫ በማመላከት እና ለኀይል እርምጃ ምቹ ሁኔታ መፍጠር በመኾኑ ይህንን ተግባራቸውን በአግባቡ ለማከናወን ፎረሙ ወሳኝ ነው ብለዋል። ፎረሙን ለማጠናከርም በዓመት 2 ጊዜ ውይይት በየሀገራቱ እየተዘዋወረ አንዲካሄድ የፎረሙን አባላት ጠይቀዋል፡፡

ዘጋቢ፡-አንዱዓለም መናን

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleደሞዝ በወቅቱ ባለመከፈሉ በኑሯቸው ላይ ጫና ማሳደሩን የሑመራ ከተማ የመንግሥት ሠራተኞች ተናገሩ።
Next article“የዉጭ ወራሪዎች ኢትዮጵያን ለመዉረር በተነሱበት ወቅት የሀገራችን ዳር ድንበር ለማስከበር የታገልን የቁርጥ ቀን ልጆች ነን ” ብርጋዴል ጀነራል ዉበቱ ጸጋየ