የባሕር ዳር ከተማ በጎ አድራጎት ማኅበር በዋግኽምራ ለተፈናቀሉ ወገኖች 3 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የተለያዩ የምግብ ድጋፍ አደረገ።

151

ሚያዝያ 07/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ባለፉት ቀናት በባሕር ዳር ከተማ በየቦታው ድንኳኖች ተዘርግተው ከከተማዋ ነዋሪዎች ለዋግ ተፈናቃዮች ድጋፍ ሲሰባሰብ ቆይቷል።

የባሕር ዳር ከተማ በጎ አድራጎት ማኅበር አባላትም የተሰባሰበውን ድጋፍ ሰቆጣ በመገኘት አስረክበዋል።

ድጋፉን ያስረከቡት የማኅበሩ ምክትል ሰብሳቢ ወጣት ተስፋየ ድረስ ፥ ማኅበሩ በባሕር ዳር ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች ላለፉት 15 ቀናት ድጋፍ ሲያሰባስብ እንደነበር ገልጿል።

ማኅበሩ በባሕር ዳር ከተማ ባዘጋጃቸው አምስት ድንኳኖች ባሰባሰበው ድጋፍ እና በውጭ ሀገር የሚገኙ በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር 3 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው የተለያዩ የምግብ እህሎችን በብሔረሰብ አሥተዳደሩ በወለህ መጠለያ ጣብያ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ መደረጉን እንደገለጸ ከዋግኽምራ ኮምዩኒኬሽን የተገኘ መረጃ ያመላክታል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደር ከአማራ ባንክ ጋር በጋራ ለመሥራት ተስማሙ።
Next articleደሞዝ በወቅቱ ባለመከፈሉ በኑሯቸው ላይ ጫና ማሳደሩን የሑመራ ከተማ የመንግሥት ሠራተኞች ተናገሩ።