ኢትዮጵያ እና ቱርክ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ዓላማ ያደረገ ውይይት አካሄዱ።

204

ባሕር ዳር: ሚያዚያ 07/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በቱርክ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አደም መሃመድ እና በቱርክ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኤርያል ማናጀር ፋኪያ አብደርህማን ከቱርክ የሲቪል አቬሽን ተጠባባቂ ዳይሬክተር ጀነራል ፕሮፌሰር ዶክተር ከማል ዬኩሱክ ጋር የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማጠናከር መክረዋል::

ከ100 ዓመታት በላይ የቆየውን የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በቀጣይነት ለማጠናከር ዓላማ አድርገው መምከራቸው ተነስቷል።

አምባሳደር አደም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ ቀዳሚ አየር መንገድ መሆኑን በማንሳት በሁለቱ ሀገራት በንግድ እና ኢንቨስትመንት ዘርፍ እየተጫወተ ያለውን ላቅ ያለ ሚና መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በሁለቱ አየር መንገዶች እ.ኤአ መስከረም 29/2021 በተፈረመው ስምምነት ውይይት በማድረግ ወደ ተግባር መቀየር አስፈላጊ በመሆኑ በሚቀጥለው ወር ወደ ኢትዮጵያ በማቅናት ከአቻቸው ጋር እንደሚወያዩ ፕሮፌሰር ዶክተር ከማል ዬኩሱክን ገልጸዋል።

ሁለቱ አየር መንገዶች ትልቁን አውሮፕላን እና ካርጎ በአዲስ አበባና በኢስታንቡል ለመጠቀም መስማማታቸው ይታወሳል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleʺአያችሁልኝን የአንበሳውን ሞት፣ በሰው እጅ መሞትን ነውር አድርጎት”
Next articleየኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደር ከአማራ ባንክ ጋር በጋራ ለመሥራት ተስማሙ።