ሚታ የተሰኘ አሠሪና ሠራተኛን የሚያገናኝ መተግበሪያ የሠራችው ተማሪ በኢንሳ እውቅና አገኘች፡፡

206

ባሕር ዳር: ሚያዚያ 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ታዳጊዋ ተማሪ በጸሎት ፍቅር ትባላለች የ12ኛ ክፍል ተማሪ ናት፡፡ ተማሪ በጸሎት እንደምትለው በሀገሪቱ በየዓመቱ በርካታ ተማሪዎች ከተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመርቀው ይወጣሉ፤ ይሁን እንጅ ተመራቂ ተማሪዎቹ በተመረቁበት ትምህርት የራሳቸውን ሥራ ለመሥራት የገንዘብ እጥረት ስለሚገጥማቸው ብዙ ጊዜ ተቀጥረው ለመሥራት ነው ጥረት ሲያደርጉ የሚስተዋሉት፡፡
ይህ ሂደትም ታዲያ በርካታ ውጣውረድ እና ተቀጥረው የሚሠሩበትን ተቋም ለማግኘት አስቸጋሪ ይኾንባቸዋል፡፡ ታዲያ ታዳጊዋ ይህን መሰረታዊ ችግር ለመፍታት የመገናኛ መረብ ፈጥሮ ወደ ሥራ በማስገባት አሰሪና ሠራተኛን ማገናኘት እንደሚያስፈልግ በማመን መተግበሪያውን ለመሥራት መነሳቷን ነው የተናገረችሁ፡፡
ተማሪ በጸሎት ብዙ ጊዜ መንግሥት በሕንጻ ኮንስትራክሽን ሥራ መሥክ ተመርቀው የሚወጡ ልጆች በራሳቸው ሥራ ፈጣሪ ኾነው እንዲሠሩ በማሰብ የሥራ ፈቃድ እንደሚሰጣቸው ገልጻ የሥራ ፈቃድ የሚወስዱት ግን ሥራ ፈልጎ ለመሥራት ስለሚቸገሩ ፈቃድ አውጥተው ለመቀመጥ እንደሚገደዱ ተናግራለች፡፡ በሌላ በኩል አሠሪዎችም ለሚያሠሩት ሕንጻ የሚፈልጉትን ባለሙያ ለማግኘት ስለሚቸገሩ በአቅራቢያቸው ያለን ሙያተኛ ለመቅጠር ይገደዳሉ፡፡ ይህ ደግሞ ለሥራ ጥራት እና ብቁ ሙያተኛ ለማግኘት አስቸጋሪ ይኾንባቸዋል ነው የምትለው፡፡
አሁን የተሠራው መተግበሪያ አሰሪዎች ሌላ ቦታ ላይ ሊያሠሩት ያሰቡትን ሥራ በቀላሉ ሥራው ባለበት ቦታ ያለን ባለሙያ በተመጣጣኝ ዋጋ ማሠራት እና የሥራ እድል በመፍጠር በኩል ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ብላለች፡፡
ሌሎች እንደ ቴሌግራም ያሉ መተግበሪያዎች ሊጠለፉ ስለሚችሉ አስተማማኝ አይደለም የምትለው ተማሪዋ እሷ የሠራችው መተግበሪያ አስተማማኝ መገናኛ እንደኾነ ነው የምትናገረው፡፡
ብዙ ጊዜ አሰሪዎች ገጠር አካባቢ ላላቸው ሥራ ወደ ገጠር ወርዶ የሚሠራላቸው ባለሙ ለማግኘት ሲቸገሩ እንደምታስተውል የተናገረችው ተማሪ በጸሎት መተግበሪያው ሥራው ባለበት አካባቢ ያለ ባለሙያን በማገናኘት ትልቅ ለውጥ እያመጣ ስለመኾኑም ተናግራለች፡፡ መረጃውን ከኢንሳ ማኅበራዊ ትስስር ገጽ አገኘን፡፡
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“የጥፋት ቡድኖችን በመደምሰስ ሰላማችንን ልናስጠብቅ ይገባል”
Next articleʺአያችሁልኝን የአንበሳውን ሞት፣ በሰው እጅ መሞትን ነውር አድርጎት”