“የጥፋት ቡድኖችን በመደምሰስ ሰላማችንን ልናስጠብቅ ይገባል”

140

ሚያዚያ 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር፣ የአፋር ክልል ዞን 5 እና የአርጎባ ብሔረሰብ አጎራባች ወረዳዎች በአፋር ክልል ዞን 5 ደዌ ወደራጌ ወረዳ የጋራ የምክክር መድረክ አካሂደዋል።
በምክክር መድረኩ ከ6 አጎራባች ወረዳዎች የተውጣጡ የሃይማኖት አባቶች፣ የሰላም ኮሚቴዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ከቀበሌ እስከ ዞን ያሉ አመራሮች ተሳትፈዋል።
በምክክር መድረኩ የተሳተፉ የሃይማኖት አባቶችና የሰላም ኮሚቴዎች በቀጣናው ያሉ አጎራባች ወረዳዎች አንድ የሚያደርጓቸው በርካታ ጉዳዮች መኖራቸውን ገልፀዋል። የጋራ ጠላታቸውን ኦነግ ሸኔንና ሌሎች የጥፋት ቡድኖችን በመለየት ቡድኖቹን ለማጥፋት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን በማጠናከር ከየወረዳ መስተዳደሮች ጋር በቅንጅት እየሠሩ መሆኑን ገልፀዋል።
የአጎራባች ወረዳ አመራሮች በበኩላቸው የአመራር ለአመራርና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቶችን በማጠናከር እስከ ቀበሌ አደረጃጀት በመፍጠር በትብብር እየሠሩ መሆኑን ገልፀዋል።
የአፋር ክልል ዞን 5 ሰላምና የሕዝብ ደኅንነት ኀላፊ ዳውድ መሀመድ የጥፋት ቡድኖችን ለሕግ ለማቅረብ በሚደረገው ትግል በቀጣናው አጎራባች ወረዳዎች ጋር በትብብር እየሰሩ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ብልጽግና ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ከድር አሊ ሰላም ሲኖር ነው ሌሎች የልማት ሥራዎችን መከወን የሚቻለውና ያገኘነውን ሰላም ለማስጠበቅ የጥፋት ቡድኖችን መደምሰስ ይገባል ብለዋል።
ዘጋቢ:–ይማም ኢብራሂም–አፋር ደዌ ወደራጌ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleበአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተላከው አጣሪ ኮሚቴ በፈተና አስተራረም ዙሪያ የደረሰበትን ሂደት ይፋ አደረገ።
Next articleሚታ የተሰኘ አሠሪና ሠራተኛን የሚያገናኝ መተግበሪያ የሠራችው ተማሪ በኢንሳ እውቅና አገኘች፡፡