“የአምንስቲ እና ሂዩማን ራይትስ ዎች ያወጡት መግለጫ በሉዓላዊነት ላይ ጣልቃ የሚገባ እና ለአንድ ወገን ያዘነበለ ነው” የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

119

አዲስ አበባ፡ ሚያዝያ 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል። አምባሳደሩ በመግለጫቸው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ ማብራሪያ መስጠታቸውን ገልጸዋል።
አምንስቲ እና ሂውማን ራይትስ ዎች የሰጡት መግለጫ በሉዓላዊነት ላይ ጣልቃ የሚገባ እና ለአንድ ወገን ያዘነበለ” መኾኑንም ገልጸዋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሬድዋን ሑሴን ከደቡብ ኮሪያ አቻቸው በኢንቨስትመንት እና በቆየው የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ላይ መወያየታቸውንም አብራርተዋል። በግብርና እና በኢንቨስትመንት ዘርፎች ደቡብ ኮሪያ ለኢትዮጵያ ድጋፍ እንደምታደርግም ገልጸዋል።
የእስራኤል የህክምና ቡድን አባለት በጦርነቱ ምክንያት የፈረሱ የጤና ተቋማትን ለማገዝ እና ለማቋቋም ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸውም በመግለጫው ተነስቷል።
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን የሚመራው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ሂደት በሳውዲ አረቢያ በአሁኑ ሂደት ከ7 ሺህ በላይ ዜጎችን መመለስ የተቻለ ሲሆን በሳመንት 3 በረራዎች እንደሚደረጉም አምባሳደር ዲና ገልጸዋል። ይህም በችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎች እስኪመለሱ ድረስ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው ያብራሩት።
ዘጋቢ፡- አንዱዓለም መናን
ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየተፈናቃዮችን የመጠለያ እና የቁሳቁስ ችግር ለመፍታት እየሠራ መኾኑን የብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
Next articleበአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተላከው አጣሪ ኮሚቴ በፈተና አስተራረም ዙሪያ የደረሰበትን ሂደት ይፋ አደረገ።