
ታሪካዊ እና የመስህብ ቦታዎች በውስጣቸው የያዙትን ታሪክ እና እውነት ለትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ጠየቁ።
“ህያው የጥበብ ጉዞ ወደ ታሪካዊቷ ሸዋ” የተሰኘ የታሪካዊ ቦታዎች ጉብኝት ዛሬ ተጀምሯል።
በጉዞው 16 የሀገር ውስጥ ጋዜጠኞች እና 26 ደራሲያን ተሳታፊዎች ናቸው።
የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ኂሩት ካሳው በሽኝት መርሀ ግብሩ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ታሪካዊ እና የመስህብ ቦታዎችን ከመጎብኘት ባለፈ በውስጣቸው የያዙትን ታሪክ እና እውነት ለትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ተጓዦቹ በሰሜን ሽዋ ከሚገኙ ታሪካዊ ቦታዎች የአፄ ሚኒሊክን የትውልድ ቦታ፣ ቤተ መንግስቱን እና ሌሎች ታሪካዊና የመስህብ አካባቢዎችንም ይጎበኛሉ።
ዛሬ ጥቅምት 5/2012 የሚጀምረው የታሪካዊ ቦታዎች ጉብኝት እስከ ጥቅምት 10/2012 እንደሚቆይ ታውቋል።
ዘጋቢ፦ በለጠ ታረቀኝ