የተፈናቃዮችን የመጠለያ እና የቁሳቁስ ችግር ለመፍታት እየሠራ መኾኑን የብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

115

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 05/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል በሚገኙ ተፈናቃዮች የሚታየውን የመጠለያ እና የምግብ ማብሰያ ቁሳቁስ ችግር ክረምቱ ከመግባቱ በፊት ቀድሞ እንደሚፈታ የብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
የብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ ዓለም አቀፍ ረጅ ድርጅቶችን በማሥተባበር የምግብ ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
የተፈናቃዮች ቁጥር ከቀን ወደ ቀን በመጨመሩ የምግብ ማብሰያ፣ የመመገቢያ ቁሳቁስ እና የመጠለያ ችግሮች መኖራቸውንም አንስተዋል፡፡ ኮሚሽነሩ እንዳሉት ተፈናቃዮች ወደ መደበኛ ኑሯቸው እስኪመለሱ የሚታዩ የመጠለያ እና የማብሰያ ችግሮችን ለመፍታት እየተሰራ ይገኛል፤ ለጎርፍ ተጋላጭ የኾኑ አካባቢዎችም ተለዋጭ የመጠለያ ጣቢያዎች ይዘጋጃሉ ብለዋል፡፡
ኮሚሽነር ምትኩ በተለይም ደግሞ በዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ከተፈናቃዮች ቁጥር መጨመር ጋር ተያይዞ 320 ካሬ ሜትር የሚሸፍኑ መጠለያ ጣቢያዎችን ለማዘጋጀት ኮሚሽኑ እየሠራ መኾኑን አንስተዋል፡፡ አጋር አካላትም እንደሚሳተፉ ነው የገለጹት፡፡ መጠለያዎቹ በቀላሉ ስለማይገኙ ከውጭ ተጓጉዘው እስኪገቡ ጊዜ የሚጠይቅ ቢኾንም ክረምቱ ከመግባቱ በፊት ቀድሞ እንደሚጠናቀቅ ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል፡፡
ኮሚሽነር ምትኩ እንዳሉት ዓለም አቀፍ ረጅ ድርጅቶች ድጋፍ ለማድረግ በፈለጉት አካባቢ እና ከፍተኛ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ድጋፍ እንዲያደርጉ መደረጉን አንስተዋል፡፡
በዚህም የዓለም ምግብ ድርጅት በሰሜን ጎንደር፣ ወርልድ ቪዥን ደግሞ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞኖች እንዲሳተፉ መደረጉን ለአብነት አንስተዋል፡፡ በቀጣይም ተጨማሪ ድርጅቶች ጋር በመነጋገር ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡-ዳግማዊ ተሠራ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleነጻነታቸውን አስጠብቀው ለመዝለቅ ትጥቃቸው ከወገባቸው ሳይፈታ፣ ዓይናቸው ከጠላት ላይ የማይነቀለው የወልቃይት ጠገዴ ሚሊሻዎች።
Next article“የአምንስቲ እና ሂዩማን ራይትስ ዎች ያወጡት መግለጫ በሉዓላዊነት ላይ ጣልቃ የሚገባ እና ለአንድ ወገን ያዘነበለ ነው” የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር