
ሚያዚያ 05/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ በግጭት ለተጎዱ አካባቢዎች የሚውል 300 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማጽደቁን አስታወቀ።
ባንኩ በዓለም የልማት ማኅበር በኩል ግጭት ለተከሰተባቸው የኢትዮጵያ አካባቢዎች ማቋቋሚያ ፕሮጀክት ድጋፍ ማጽደቁን አመልክቷል።
ፕሮጀክቱ መሠረታዊ አቅርቦቶችን፣ የመሠረተ ልማት ግንባታዎችን፣ የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎችን ያካተተ መኾኑንም ባንኩ ገልጿል።
በተጨማሪም ፕሮጀክቱ ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች ጾታዊ ጥቃትና የሥነ ልቦና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ እንደሚያደርግ ተነግሯል።
እንደ ኢዜአ ዘገባ ፕሮጀክቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ እንደሚከናወን የተገለጸ ሲኾን በዋናነት በአማራ፣ አፋር፣ ኦሮሚያ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝና ትግራይ ክልሎች እንደሚተገበር ተመልክቷል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/