
ደብረ ብርሃን : ሚያዝያ 05/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ማኅበራዊና ልማት ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በተለያዩ ምክንያቶች ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ከ58 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ድጋፍ ማድረግ መጀመሩን አስታውቋል።
ጽሕፈት ቤቱ ድጋፍ እያደረገ የሚገኘው በዞኑ በሚገኙ ስድስት ወረዳዎች እና ከተማ አሥተዳደሮች መኾኑን አስታውቋል። ድጋፉ በመጠጥ ውኃ፣ ንፅህና አጠባበቅ፣ በምግብ እና ምግብ ነክ ባልሆኑ ዘርፎች ነው ተብሏል።
የጽሕፈት ቤቱ ኀላፊ አቶ አማን ደግፍ በጦርነቱ የተጎዱ ወገኖችን በመለየት ድጋፉ እየተደረገ መኾኑን ገልጸዋል።
ጽሕፈት ቤቱ አስቀድሞ በሠራው የጉዳት ዳሰሳ 130 ሺህ የሚደርሱ ወገኖችን ተደራሽ ለማድረግ ያለመ ድጋፍ መጀመሩን አስታውቀዋል።
ኀላፊው ከ58 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ከአጋር አካላት ተገኝቶ ወደ ሥራ ተገብቷል ነው ያሉት።
በኤፍራታና ግድም እና ቀወት ወረዳዎች የዓይነት ድጋፎችን አድርጓል።
ዘጋቢ፡-ኤልያስ ፈጠነ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/