የዓለም ማኅበረሰብ ወደ ቅዱስ ላልይበላ ቅርስ እንዲመለከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ ጥሪ አቀረቡ፡፡

155

ሚያዝያ 04/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ወደ ቅዱስ ላልይበላ ዓለም አቀፍ ቅርስ እንዲመለከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ ጥሪ አቀረቡ፡፡
በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እና በነበረው ጦርነት የቅዱስ ላልይበላ ቅርስ የቱሪዝም እና የከተማው እንቅስቃሴ ከፍተኛ ጫና ውስጥ መውደቁን ገልጸዋል።
የችግሩን ስፋት እና ጥልቀት በመገንዘብ ኹሉም ኢትዮጵያዊ ለድጋፍ እጁን እንዲዘረጋም ጥሪ ማቅረባቸውን ፋብኮ ዘግቧል፡፡
የቅዱስ ላልይበላ ዓለም አቀፍ ቅርስ ለኢትዮጵያ ሐብት ፣ ለሕዝቧም ኩራት፣ ለቤተ ክርስቲያኗም ከፍተኛ የመንፈሳዊ ጥበብ ውጤትና መገለጫ በመኾኑ መንግሥትን ጨምሮ ሌሎች መንግሥታዊ ያልኾኑ ተቋማት ችግሩን ለመቅረፍ ሊረባረቡ ይገባል ብለዋል፡፡
በገዳሙ የውስጥ ገቢ ተጀምሮ የነበረው የቅርስ ልማት ማለትም የመካነ ቅርሱ አጥርና በር፣ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች፣ የመሬት ማስተካከልና የዛፍ ተከላ፣ ከአብያተ ክርስቲያናቱ ጋር እኩል ዘመን ያላቸውና በባሕላዊ አቀማመጥ ችግር እየደረሰባቸው ያሉ ተንቀሳቃሽ ቅርሶች፣ እንቁ፣ ከወርቅ፣ ከብር፣ ከነሐስ፣ ከመዳብ፣ ከብረት፣ ከድንጋይ፣ ከሸክላ፣ ከእንጨት፣ ከቆዳ እና ከሌሎች ማዕድናት የተሠሩ ቅርሶች ማስቀመጫ ደረጃውን የጠበቀ ቤተ መዛግብት (ዘመናዊ ሙዚየም) ግንባታ ለማስፈፀም ከአቅም በላይ በመኾኑ የድርሻችንን በመወጣት ቅርሳችን እንጠብቅ የሚል መልዕክት በጊዜያዊ የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴው ተላልፏል፡፡
የባንክ ሂሳብ ቁጥር ፡- በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ አቢሲኒያና ዳሽን ባንኮች በ0712 የባንክ የሒሳብ ቁጥር ለቅዱስ ላልይበላ ገዳም ዓለም አቀፍ ቅርስ ዜጎች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0911061164 እና 0913912457 መደወል እንደሚቻል ተገልጿል፡፡
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“ዓለም አቀፍ ተቋማትና የረድኤት ድርጅቶች በአፋርና አማራ ክልል ያለውን ከፍተኛ የሰብዓዊ ቀውስ ዘንግተውታል” አሜሪካዊቷ ጋዜጠኛ አን ጋሪሰን
Next articleቺርቤዋ ሜጋቢት 30-7-2014 ም.አ