
ባሕር ዳር: ሚያዚያ 04/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ዓለም አቀፍ ተቋማትና የረድኤት ድርጅቶች በአፋርና በአማራ ክልል ያለውን ከፍተኛ የሰብዓዊ ቀውስ ሊገነዘቡና አስፈላጊውን ድጋፍ ሊያደርጉ ይገባል ስትል አሜሪካዊቷ ጋዜጠኛ አን ጋሪሰን ተናገረች።
ሂዩማን ራይትስዎችና አምነስቲ ኢንተርናሽናል በቅርቡ በሰሜኑ ኢትዮጵያ ተከስቷል ያሉትን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በተመለከተ ያወጡት የጋራ ሪፖርትም ፖለቲካዊ ይዘት አለው ብላለች።
አን ጋሪሰን በኢትዮጵያ በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎች ያደረገችውን ጉብኝት አስመልክቶ ከኢዜአ ጋር በነበራት ቆይታ ጦርነቱ ከፍተኛ የሰብዓዊ ቀውስ ማስከተሉን ገልጻለች።
አሸባሪው ሕወሓት በሰው ህይወት ላይ ካደረሰው ጉዳት በተጨማሪ የተለያዩ መሰረተ ልማቶችን ማውደሙንና ይህም በርካታ ሰዎች በሰብዓዊ ቀውስ ውስጥ እንዲቆዮ አድርጓቸዋል ብላለች።
ይህንንም ተከትሎ አሸባሪው የሕወሓት ቡድን በሕዝቡ ላይ የፈጸመው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት እጅግ አሰቃቂ መሆኑን ተዘዋውራ በተመለከተቻቸው ሥፍራዎች ባደረገችው ምልከታ ማረጋገጧን ጠቁማለች።
ያም ሆኖ ዓለም አቀፍ ተቋማትና የረድኤት ድርጅቶች በአማራና በአፋር ክልል ያለውን የሰብዓዊ ቀውስ ዘንግተውታል፤ የሚያደርጉትም ድጋፍ ከሚጠበቀው በታችና ሁሉን አቀፍ አለመሆኑን አመልክታ በኢትዮጵያ ያለው የሰብዓዊ ቀውስ በትግራይ ብቻ ሳይሆን በአፋርና በአማራ ክልል መኖሩን በማወቅ ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚገባ ትናግራለች።
በሌላ በኩል ሂዩማን ራይትስ ዎች እና አምነስቲ ኢንተርናሽናል በቅርቡ በሰሜኑ ኢትዮጵያ ተከስቷል ያሉትን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በተመለከተ ያወጡት የጋራ ሪፖርትም ፖለቲካዊ ይዘት አለው ብላለች።
ሪፖርቱ የወጣው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በጉዳዩ ላይ ያጠናውን ሪፖርት ከመለቀቁ ከቀናት በፊት መሆኑን በማንሳት፤ ይህም አንድ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት በማለም የተደረገ መሆኑን ገልጻለች።
ከዚህም በላይ ሪፖርቱ የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ ማዕቀብ እንዲጥሉ ሁኔታዎችን ለማመቻቸትና ማዕቀብ ካልተጣለ በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ሊባባስ ይችላል የሚል እምነት በሰዎች ውስጥ እንዲያድር ያለመ መሆኑንም ነው ያነሳችው።
ሂዩማን ራይትስ ዎች፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናልና የዓለም ጤና ድርጅት በኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ እንዲጣል በአሜሪካን መንግሥት ውስጥ ያሉ የአንዳንድ ግለሰቦች ፍላጎትን ለማስፈጸም እየሰሩ መሆኑንም ጠቁማለች።
በተለይም የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ጄነራል የሆኑት ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ስለ ትግራይ የሰብዓዊ ቀውስ ብቻ በተደጋጋሚ የሚያደርጉት ውግንና የፖለቲካ አቋማቸውን አመላካች ነው፣ይህም ገለልተኛ በመሆን ድርጅቱን ለመምራት ከገቡት ቃል ጋር የሚጻረር ነው ብላለች።
በኢትዮጵያ ያለውን የሰብዓዊ ቀውስና ሌሎች ፖለቲካዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ትክክለኛ መረጃዎች በማሰራጨት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የኢትዮጵያን እውነታ እንዲረዳ የበኩሏን እንደምትሰራ አን ጋሪሰን ተናግራለች።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/