
ባሕር ዳር: ሚያዚያ 04/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ከተማ ምክር ቤት በ23ኛ መደበኛ ጉባኤው የተቋማትን የእቅድ አፈጻጸም ገምግሞ አቅጣጫ አስቀምጧል።
ምክር ቤቱ 4ኛ ዙር ምርጫ 10ኛ ዓመት የሥራ ዘመን በ23ኛ መደበኛ ጉባኤው የከተማ አስተዳደሩን የሰላምና ደኅንነት የእቅድ አፈጸጸም ሪፖርትን አዳምጧል።
በከተማ አስተዳደሩ ሰላምና ደኅንነት ሪፖርት መሰረት:-
✍️የባሕር ዳር ከተማ ወጣቶች በህልዉና ዘመቻው በተለያዩ የጸጥታ አደረጃጀቶች ተሳትፈው ለሀገር እና ለክልልም አኩሪ ጀብድ መፈጸማቸው።
በሌላ በኩል የከተማ አስተዳደሩ ሰላምና ደኅንነት ሪፖርት እንደሚያሳየው ስግብግቦችም ችግሮችን እንደመልካም አጋጣሚ ተጠቅመው በሕገውጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው የቆዩ ቢኾንም እርምጃም ተወስዷል።
በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ባዬ አለባቸው የቀረበውን ጥቅል ሪፖረት እና የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ አባላት የመስክ ምልከታ ግምገማን ምክርቤቱ አዳምጧል፡፡
የምክር ቤት አባላቱ ሪፖርቱን መሰረት በማድረግ ሀሳባቸውን ሰጥተዋል፡፡
✍️ለረጅም ጊዜ ታጥረው የተቀመጡ የኢንቨስትመንት ቦታዎች ጉዳይ አሳሳቢ እየኾነ ስለመምጣቱና ላልተፈለገ ዓላማም እየዋለ ነው ብለዋል።
✍️ከሪልስቴት ጋር በተያያዘ ግልጽነት የጎደለው መረጃ እየወጣ ነው፣ አደናጋሪ የኾኑ መረጃዎችን ማጥራት ይገባል፣ ለሙስናና ብልሹ አሠራር የሚዳርጉ ድርጊቶች ታይተዋል ነው ያሉት።
✍️ከቤት ማኅበር ጋር በተያያዘ በየማኅበሩ የሚደራጁ ሕገወጥ አባላት አሉ፣ጉዳዩ ከፍተኛ ሙስና የሚታይበት ዘርፍ ኾኗል የሚሉ አስተያየቶችም ተሰጥተዋል።
✍️የመኖሪያ ቤት ኅብረት ሥራ ማኅበራትም በዚህ ዓመት ባቀደው ልክ አልሠራም ብለዋል። ካሳ ለከፈሉ ማኅበራት እስካሁን ቦታውን በእጃቸው ማስገባት አለመቻሉም ተነስቷል።
✍️መመሪያው የመኖሪያ ቤት ማኅበር አባላት ካሳ በከፈሉ በ27 ቀን ውስጥ ቦታቸውን ሸንሽኖ ያስረክባል የሚል ቢኾንም ምክንያቱ በግልጽ ባልታወቀ ጉዳይ ሁለት ወራትን ተሻግሯል ነው የተባለው።
የሕግና አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ አባላት በበኩላቸው በመሥክ ምልከታ ያረጋገጡትን መልካም ተሞክሮ እና ሊስተካከሉ ይገባቸዋል ያላቸውን ሀሳቦች አንስቷል፡፡
በመልካም ሊነሱ ይገባቸዋል የተባሉትም፡-
✍️የፖሊስ አካላት ላይ በተደረገ ግምገማ የዜጎች መብት አያያዝ የተሻለ ኾኖ ተገኝቷል፡፡
✍️ሕዝባዊ መሰረቱን የጠበቀ ሚሊሻ ተገንብቷል።
✍️ሕግ በማስከበር ተግባር ፖሊስ ከመከላከያና ከልዩ ኀይል ጋር ጥሩ ቅንጅዊ አሠራር መፍጠር መቻሉ የሚሉ ይገኙበታል።
ሊስተካከሉ ይገባቸዋል በሚል የተነሱትም፡-
✍️በጸጥታ አካሉ ትኩረት ማነስ በቀን የሚፈጸም ዝርፊያ እና ቅሚያ መታየቱ፡፡
✍️በስውር የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ጥልቅ ምርመራ አለመደረጉ፡፡
✍️አንዳንድ የጸጥታ አባላት ከሌባ ጋር መተባበራቸው፣ የኢግዚቢት ንብረትን ለግል ማድረግ፣ በሕገወጥ መንገድ መዝገብ ማዘጋት፣ በሙስና ወንጀል የተጠለፉ የጸጥታ አካል መታየታቸው፣ በማረሚያ ቤቶችም ታራሚን የሚያስመልጡ የጸጥታ አካላት መገኘታቸው፣ ሚስጥር አባካኝነት መኖሩ የሚሉ የግምገማ ሃሳቦች በቋሚ ኮሚቴ አባላቱ ቀርበዋል።
በኢኮኖሚ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በኩል የቀረቡ ግምገማዎች ደግሞ፡-
✍️የመሰረታዊ ሸቀጦች የዋጋ ንረት ነገር መፍተሔ ማጣቱ
✍️የኅብረት ሥራ ማኅበራት የኑሮ ውድነቱን መግታት የሚችል አቅም የሌላቸው መኾናቸው።
✍️ኅብረት ሥራ ማኅበራትን ማጠናከረም መቆጣጠርም እንደሚያስፈልግ ተነስቷል።
✍️የከተማውን የነዳጅ ችግር ለመፍታት በሚል የተሰጠው የነዳጅ ማደያ ግንባታ ፈቃድ ችግር ፈች መኾን አለመቻሉ።
✍️ከ11ዱ የነዳጅ ማደያ ግንባታ ቦታዎች አንድ ማደያ ብቻ በትክክል ወደ ሥራ ሲገባ ቀሪዎቹ ታጥረው መቀመጣቸው ተገቢ አለመኾኑ።
✍️አስቀድሞም በከተማዋ ከነበሩት 18 ነዳጅ ማደያ ዲፖዎች በተጨማሪ ለ11ማደያዎች ቦታ መስጠቱ ስህተት እንደነበር፤ በከተማዋ የነዳጅ አቅርቦት እንጂ የነዳጅ ማደያ እጥረት እንዳልነበር የግምገማ ሃሳብ ቀርቧል።
ምክር ቤቱ ዛሬ በሚኖረው የሁለተኛ ቀን ውሎው ቀሪ አጀንዳዎች ላይ ውይይት ያደርጋል፤ ከአባላቱ የሚነሱ ጥያቂዎች ላይም ምላሽ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።
ዘጋቢ:- ጋሻው አደመ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/