የአፍሪካ ልማት ፈንድ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለ4 ሀገራት ታዳሽ ኀይል ማስፋፊያ 5 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አጸደቀ።

80

ሚያዝያ 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአፍሪካ ልማት ፈንድ የዳይሬክተሮች ቦርድ ድጋፉን ያጸደቀው በምሥራቅ አፍሪካ ማለትም በኢትዮጵያ፣ በኤርትራ፣ በጅቡቲ እና በሱዳን በረሃማ አካባቢዎች ለሚኖሩ ሰዎች የኤሌክትሪክ ኀይል እንዲያገኙ ነው።

ድጋፉ በሀገራቱ በርሃማ አካባቢዎች የታዳሽ ኀይል ለማምረት የሚደረገውን እንቅስቃሴ ለመደገፍ የተደረገ መኾኑን ቦርዱ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

አሁን የተደረገው ድጋፍ የአፍሪካ ልማት ፈንድ ለሕዝብ አገልግሎት እንዲሰጡ ከሚደግፋቸው 15 ፕሮጀክቶች አንዱ ሲኾን ለሀገራቱ የኤሌክትሪክ ኀይል ተደራሽ እንዲሆን በፀሐይ ኀይል የሚመረት ኀይል ፓርክ ጥናትን፣ ሀገራቱን በኀይል የሚያስተሳስር የኀይል ቋት ግንባታን፣ ከፍተኛ ኀይል የሚሸከም ገመድ ዝርጋታን ያካተተ መኾኑ ተመልክቷል።

ድጋፉ በቀጠናው የታዳሽ ኀይል ማበልጸግ ላይ የሚስተዋለውን ክፍተት የሚሞላ ከመኾኑም በተጨማሪ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚከሰትን ችግር ለመቀነስ የራሱን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት መገለጹን የኢዜአ ዘገባ ያመላክታል።

በርሃን ወደ ታዳሽ ኀይል መቀየር የሚለው ፕሮጀክት 10 ጌጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኀይል በማመንጨት እ.ኤ.አ እስከ 2030 ድረስ ለ250 ሚሊየን ሕዝብ ተደራሽ ማድረግን ታሳቢ ያደረገ መኾኑ ተጠቁሟል፡፡

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleStatement on the Joint Investigation Report of Amnesty International and the Human Rights Watch
Next articleመስኖ በምግብ ራስን ለመቻል አማራጭ የሌለው ምርጫ እንደኾነ መገንዘብ እንደሚገባ የግብርና ቢሮ ገለጸ፡፡