“ሕዝቡ የሰላም እጦትና ጦርነት አንገሽግሾታል” ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ

464

ባሕር ዳር: ሚያዚያ 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ሕዝቡ የሰላም እጦትና ጦርነት አንገሽግሾታል፣ ከባድ መስዋእት ከፍሏል ከዚህ መውጣት ይፈልጋል ሲሉ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ገልጸዋል።

ለብሔራዊ መግባባት ውይይቱ ስኬታማነት በሀገር ውስጥና በተለያዩ የውጭ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሙሉ መብታቸውን ሊጠቀሙና ኀላፊነታቸውን ሊወጡም ይገባል ነው ያሉት፡፡

ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን ለኢፕድ እንደገለጹት ለብሔራዊ መግባባት ውይይቱ ስኬታማነት ሁሉም መብቱን ሊጠቀምና ኀላፊነቱን ሊወጣ ይገባል።

“ወሳኙ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው፤ ሕዝቡ የሰላም እጦትና ጦርነት አንገሽግሾታል፣ ከባድ መስዋእት ከፍሏል ከዚህ መውጣት ይፈልጋል” ብለዋል።

ሁሉንም ነገር ብሔራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ይፈታዋል ብሎ መጠበቅ የዋህነት ነው ያሉት ዋና ኮሚሽነሩ የኮሚሽኑ ተግባር አስቻይ ሁኔታዎችን መፍጠርና ማመቻቸት ነው፤ ውሳኔና ኀላፊነቱ የሕዝቡ ነው ብለዋል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleበኩር ጋዜጣ ሚያዝያ 03/2014 ዓ.ም ዕትም
Next articleTigrayan exceptionalism has led to the war, and is now hindering peace