“ከሕገወጦች የተያዘው ከ750 ሺህ ሊትር በላይ ዘይት ለሕብረተሰቡ ተከፋፍሏል” የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ

140

ባሕር ዳር: ሚያዚያ 02/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በከተማዋ በተለያዩ ጊዜያት በተደረገ የቁጥጥር ሥራ ከሕገወጦች የተያዘው ከ750 ሺህ ሊትር በላይ ዘይት ለሕብረተሰቡ መከፋፈሉን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታውቋል። ቢሮው የዘይት አቅርቦት ማነስና የዋጋ መጨመር ችግሮችን በፍጥነት ለመፍታት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመስራት ላይ እንደሚገኝም ገልጿል።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ አቶ አደም ኑሪ ለኢፕድ እንደተናገሩት ቢሯቸው በተለያዩ ጊዜያት ባደረገው የቁጥጥር ሥራ ከሕገወጦች የያዘውን ከ750 ሺህ ሊትር በላይ ዘይት ለሕብረተሰቡ ማከፋፈል ችሏል። ሕገወጥ ነጋዴዎቹ ዘይቱ የተወረሰባቸው ገበያው እየፈለገው በሚፈለው ፍጥነት ወደ ገበያ ባለማቅረባቸውና የዘይት ምርቱ አዲስ አበባ ከተማ ገበያ መቅረብ እያለበት ወደ ተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ሲጭኑ በመገኘታቸው ነው።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮም ዘይቱን ከነጋዴዎቹ በመውሰድ ለሸማች ሕብረት ሥራ ማሕበራት ማስረክቡን አመልክተው፤ ማሕበራቱ ዘይቱን ለሕብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ ማከፋፈላቸውንም አቶ አደም ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በቅርቡ የተከሰተውን የዘይት አቅርቦት ማነስና የዋጋ መጨመር ችግሮችን በፍጥነት ለመፍታትም ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየኢትዮጵያ አየር መንገድ “ከኢድ እስከ ኢድ ወደ ሀገር ቤት ” የትኬት ዋጋ ላይ የ20 በመቶ ቅናሽ አደረገ።
Next articleአምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሂዩማን ራይትስ ዎች በጋራ ያወጡትን ሪፖርት እንደማይቀበለው የአማራ ክልል መንግሥት አስታወቀ።