ከሕዝብ የተነሱ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ለመመለስ እየሠራ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ።

185

ባሕር ዳር: ሚያዚያ 02/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በመላው ሀገሪቱ በተደረጉ ውይይቶች ከሕዝብ የተነሱ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ደረጃ በደረጃ ለመመለስ እየተሠራ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር እዮብ ተካልኝ ለኢፕድ እንደገለጹት በቅርቡ በተደረጉ ሕዝባዊ ውይይቶች ከኢኮኖሚ ጋር በተያያዘ ከሕዝብ በርካታ ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡ ሕዝቡ ያነሳቸውን ጥያቄዎችም በየደረጃው ለመመለስ መንግሥት ትኩረት አድርጎ እየሠራ ይገኛል ብለዋል፡፡

ከሕዝብ የኑሮ ውድነት፣ ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል፣ የውኃና መብራት መሰረተ ልማቶች ላይ ያሉ ክፍተቶችና አገልግሎት አሰጣጦች ላይ ያተኮሩ ጥያቄዎች ተነስተዋል ያሉት ዶክተር እዮብ፤ በተለይ ከኑሮ ውድነት ጋር በተገናኘ የተነሱ ችግሮች በቶሎ መፈታት እንዳለባቸው ጠቅሰዋል።

የኑሮ ውድነቱን ለመፍታት ከፍተኛ ሥራ ይጠይቃል፤ ይህን ሥራ በየደረጃው ያለው አመራር ሕዝብን አስተባብሮ መሥራት አለበት ነው ያሉት፡፡ ዘይት ላይ የነበረውን እጥረት ለመፍታት ባልተለመደ መልኩ መንግሥት በቀጥታ ገብቶ ግዢ እንዲፈጸም መደረጉንም ገልጸዋል። በዚህም መሰረት 12 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱንና በየወሩ የ50 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ግዢ ለመፈጸም ተወስኖ እየተሠራ መሆኑን አስታውቀዋል።

ይህም በተወሰነ ደረጃ የጠፋውን የዘይት ምርት የማረጋጋት ዕድል እንዳለው ተናግረዋል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleአምባሳደር ታዬ ከአውሮፓ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጋር በወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ እና በአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸውን አስታወቁ።
Next articleየኢትዮጵያ አየር መንገድ “ከኢድ እስከ ኢድ ወደ ሀገር ቤት ” የትኬት ዋጋ ላይ የ20 በመቶ ቅናሽ አደረገ።