
ባሕር ዳር: መጋቢት 30/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) 80ኛ ዓመቱን በባሕር ዳር እያከበረ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የተመሰረተው በ1934 ዓ.ም ነው። ኢዜአ ከምስረታው ጀምሮ ስያሜውና አደረጃጀቱን በመለዋወጥ የተለያዩ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
በመላ ሀገሪቱ ከ35 በላይ ቅርንጫፎቹ አዲስ አሠራርና አደረጃጀቶችን ተግባራዊ አድርጓል። ኢዜአ የህልውናውን ዘመቻ፣ የታላቁ የህዳሴ ግድብ፣ የኮሮናቫይረስ መከላከል እና ዋና ዋና ሀገራዊ ኹነቶችን ከቦታው በመዘገብ የዜና ምንጭ በመኾን አገልግሏል።

ኢዜአ በሀገሪቱ ለሚገኙ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ጣቢያዎች፣ የማኅበረሰብ ሬድዮኖች፣ለጋዜጦች እና ለተለያዩ የውጭ መገናኛ ብዙኃን የዜናና ዜና ነክ ዘገባዎች ምንጭ በመኾን እየሠራ እንደኾነ ተገልጿል።
በበዓሉ ላይ የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር) ኢዜአ በከተማ አሥተዳደሩ በፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያ ኹነቶችን በመዘገብ ሲያገለግል መቆየቱን ተናግረዋል። ከተማ አሥተዳደሩ ለተቋሙ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋልም ነው ያሉት።

የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኀላፊ ግዛቸው ሙሉነህ ኢዜአ በክልሉ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘገባዎችን ለተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን በመስጠት እያገለገለ መኾኑን ተናግረዋል። ኢዜአ የተፈጠሩትን ቀውሶች በማርገብ፣ ለውጡ ወደ ፊት እንዲራመድ በማድረግ፣ ሚዛናዊ ዘገባ በመሥራትና ነፃ ሚዲያ በመኾን እየተንቀሳቀሰ መኾኑን አስረድተዋል።
አቶ ግዛቸው እንዳሉት ኢዜአ አንጋፋነቱን ተጠቅሞ ለሌሎችም ሚዲያ አስተማሪ ኾኖ እንዲቀጥል የክልሉ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል፣ ተቀራርቦም ይሠራል። ኢዜአ በአማራ ክልል ስቱዲዮ በመገንባት የዜና ማእከል በመኾን ዘገባን ሊያሰራጭ እንደሚገባ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሰይፈ ደርቤ እንዳሉት ኢዜአ ኢትዮጵያ ከፋሽስት ጣሊያን ነፃ በወጣችበት ወቅት የኢትዮጵያ ብቻ ሳይኾን የአፍሪካውያን ድምፅ በመኾን አገልግሏል። የዜጎችን የልማት ተጠቃሚነት በማረጋገጥ፣ ሀገራዊ መግባባት እንዲፈጠር ከመሥራት ባለፈ የኢትዮጵያን ገጽታ በመገንባት ሲያገለግል እንደቆየም ዋና ሥራ አስፈጻሚው አስገንዝበዋል። ኢዜአ ዘመናዊ የሚዲያ ኮምፕሌክስን በማሟላት የአፍሪካ ድምፅ ለመኾን እየሠራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።
ዘጋቢ:- ቡሩክ ተሾመ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
