
ባሕር ዳር: መጋቢት 29/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአዲስ አበባ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ነፍሰጡር ሴቶች፣ የሚያጠቡ እናቶችንና ሕጻናት የአልሚ ምግብ ድጋፍ ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል ሥምምነት ተደረገ።
ሥምምነቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ሕጻናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ነው ከተለያዩ ተቋማት ጋር ዛሬ የተፈራረመው።
ሥምምነቱን የቢሮው ኃላፊ ዶክተር ሃና የሺንጉስ እና አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የቀዳማይ ልጅነት እድገት ኮሚቴ ሰብሳቢ ከአቶ ጃንጥራር አባይ፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኅብረት ሥራ ማኅበራት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው አሊና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ ተወካይ አቶ ግርማ ገዲ ተፈራርመዋል።
ሥምምነቱ በዝቅኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ነፍሰጡር ሴቶች ፤የሚያጠቡ እናቶችና እድሜያቸው እስከ ሦስት ዓመት ለሚደርሱ ሕጻናት በመዲናዋ በሚገኙ በተለያዩ የኅብረት ሥራ ሸማቾች አማካኝነት የአልሚ ምግቦች ለማቅረብ ያስችላል ተብሏል።
የቢሮው ኃላፊ ዶክተር ሃና የሺንጉስ ይህም የሕጻናት በአእምሮ እና በሥነ-ልቦና የተሻሉ እንዲሆኑ እንዲሁም በሕጻናት ላይ የሚታየውን የመቀንጨር ብሎም በእድገታቸው ላይ የሚስተዋለውን ዘርፈ ብዙ ችግር ለመቅረፍ ያስችላል ብለዋል።
ለመርኃ ግብሩ 40 ሚሊየን ብር በመመደብ በ11 ክፍለ ከተሞች ለሚገኙ 9 ሺህ ነፍሰጡር ሴቶች፤ አጥቢ እናቶችና እድሜያቸው እስከ ሦስት ዓመት ለሚሆኑ ሕጻናት አልሚ ምግቦችን በተለያዩ የሸማቾች ኅብረት ሥራ ማኅበራት አማካኝነት እንደሚደረግ ጠቁመዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የቀዳማይ ልጅነት መርኃ ግብር ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ጃንጥራር አባይ ነፍሰጡሮች፣ አጥቢ እናቶችንና ሕጻናትን ጤናማ እንዲሆኑ ከተፈለገ አልሚ ምግቦችን እንዲያገኙ የማድረግ ሥራ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።
ለእነዚህም አካላት የሚቀርቡ አልሚ ምግቦች ተገቢውን የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ እንዲሆኑና ቀጣይነት ባለው መልኩ ተደራሽ የማድረግ ሥራ መሥራት ይጠይቃል ሲሉ ተናግረዋል።
የሸማች ማኅበራት የሚያቀርቡትን አልሚ ምግቦች አቅርቦታቸውን ሳያቆራርጡ በወቅቱ ለተጠቃሚዎች እንዲያቀርቡ አሳስበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኅብረት ሥራ ማኅበራት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው አሊ፤ አልሚ ምግቦች የተጠቃሚዎቹ በፍጥነት ለማቅረብ በቅንጅት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
