የሃይማኖት አባቶች ትልቅ ተሰሚነት ስላላቸው የሃይመኖት መቻቻልና መልካም ሰብዕናን በትውልዱ ላይ ለማስረጽ በትኩረት እንዲሠሩ ተጠየቀ።

322

አዲስ አበባ፡ መጋቢት 29/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ የሃይማኖት መቻቻልን እና መልካም ሰብዕና መገንባት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ የመንግስት የሥራ ኀላፊዎች፣ ምሁራን እና ወጣቶች በተገኙበት ከሃይማኖት አባቶች ጋር ውይይት እየተካሄደ ነው ።
የሃይማኖት ተቋማት ትውልድንና ሀገርን ለመገንባት መልካም እሴቶችን እና የሀገር ፍቅርን ለማስጠበቅ ትልቅ ሚና ስላለው የሃይማኖት አባቶችና ተቋማት ሚናቸው ሰፊ መኾን እንዳለበት በውይይቱ ተነስቷል ።
የሃይማኖት አባቶች ትልቅ ተሰሚነት ስላላቸው ግጭቶችን ለመመፍታት ሰፊ ሚና በመጫወት የሃይመኖት መቻቻልና መልካም ሰብዕናን በትውልዱ ላይ ለማስረጽ በትኩረት እንዲሠሩ ተጠይቋል።
የራሱን ሃይማኖት የሚወድና የሚያከብር አማኝ የሌሎችንም በማክበር የሃይማኖት መቻቻልን ማሳደግ ይኖርበታል ፤ የሎሎችን እምነት በማጣጣል፣ የሎሎችን እምነት ባልተገቡ ድርጊቶች ና ንግግሮች በማንሳት መቻቻሎች እንዳይኖሩ ማድረግ የለባቸውም ሲሉም ውይይቱ ላይ የተገኙ ተሳታፊዎች አንስተዋል ።
ይቅርታ በመባባል አንድነትን ማሳደግና ግጭቶችን መፍታት እንችላለን ፤ ስለዚህም አሁን ኢትዮጵያ ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ በመረዳት እና ችግሮችን በመፍታት ሀገርን ለመገንባት የእምነት ተቋማት ያላቸው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ የተለያዩ የሃይመኖት ተከታዮችን የእምነት አባቶች መልካም ሰብዕናን በማስተማር የሃይመኖት መቻቻልን ማሰድግ ይጠበቃል ተብሏል በውይይቱ።
ዘጋቢ- ራሔል ደምሰው
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“23 ፕሮጀክቶች መሬታቸውን በመንጠቅ ወደ መሬት ባንክ እንዲመለስና ለሌሎች አልሚዎች እንዲተላለፍ ተደርጓል” የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር
Next article“በወልቃይት ጠገዴና ጠለምት አማራ ሕዝብ ላይ በአሸባሪው ህወሃት የተፈጸመውን ግፍ ዓለም ሊያውቀው ይገባል” በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት አጥኝ ቡድን