
ጎንደር: መጋቢት 29/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተቋቋመው የፐብሊክ ዲፕሎማሲና ዓለምአቀፍ ጥናት ማዕከል በዕውቀትና በምርምር በዳበሩ መረጃዎች ላይ ተመስርቶ በየጊዜው በሀገራችን ላይ የሚደረጉ የውጭ ሀገራት የተሳሳቱ ጫናዎችን ለማረምና እየገጠሙ ያሉ የዲፕሎማሲ ችግሮችን መቅረፍ ቀዳሚ ዓላማው ነው ተብሏል።
በመርኃ ግብሩ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ባደረጉት ንግግር የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ወቅቱ የሚጠይቀው የዲፕሎማሲ ስልት መኾኑን ጠቁመዋል። የጎንደር ዩኒቨርሲቲም በእውነተኛ መረጃዎች ላይ የተመሰረቱ የሀገራችን መልካም ገጽታን ማጉላት የሚያስችል የፐብሊክ ዲፐሎማሲና ዓለም አቀፍ ጥናት ማዕከል መክፈቱ ዘርፈ ብዙ ጥቅም እንዳለው ተናግረዋል።
ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኹሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ማዕከላት እንዲከፈቱ እየሠራ እንደሚገኝ እና ከአኹን በፊት በቦንጋ እና አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲዎች መከፈቱን አንስተዋል፡፡
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር አስራት አጸደወይን የሀገራት ጥንካሬ የሚለካው ባላቸው ወታደራዊ አቅም ብቻ ሳይኾን አማላይ የባሕልና እምቅ ሕዝባዊ ዕሴቶችን በማስተዋወቃቸው መኾኑን ተናግረዋል፡፡
የጎንደር ዩኒቨርሲቲም ማዕከሉን ለማስጀመር ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን የተናገሩት ዶክተር አስራት ለሀገር ውስጥና ለውጭ ማኅበረሰብ የኢትዮጵያ ትክክለኛ ገጽታ ለማስተዋወቅ በትኩረት እንደሚሠራም አስረድተዋል።
በመርኃ ግብሩም በጎንደር ፋሲለደስ ኪነት ቡድን የተዘጋጀው” ለዛ ዓባይ ኅብረ ዝማሬ” ተመርቋል።
ኅብረ ዝማሬው የኢትዮጵያውያን ኩራት፣ ሃብትና የጥንካሬ መገለጫ በኾነው በዓባይ ወንዝ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነው።
ዘጋቢ፡-ኃይሉ ማሞ-ከጎንደር
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/