የሚኒስትሮች የጋራ ግብረ ኀይል እስካሁን የተካሄዱ የምርመራና የመልሶ ማቋቋም ሥራን እየገመገመ ነው።

145

መጋቢት 28/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የሚኒስትሮች የጋራ ግብረ ኀይል እስካሁን የተካሄዱ የምርመራና የመልሶ ማቋቋም ሥራን በገመገመበት መድረክ በአማራ፣ አፋር እና ትግራይ ክልሎች የተፈፀሙ ወንጀሎችን ተመልክቷል።
ግብረ ኀይሉ በሥሩ የተዋቀሩ ኮሚቴዎች እየሠሯቸው ያሉ ተግባራትን እና ሥራዎቹ ያሉበትን ደረጃ ነው እየገመገመ ያለው።
በሰሜኑ ኢትዮጵያ ክፍል የተከሰተው ጦርነት ተከትሎ በሦስቱም ክልሎች ማለትም በአማራ፣ አፋር እና ትግራይ ክልሎች የተፈፀሙ ወንጀሎችን እንዲሁም የመልሶ ማቋቋም ሥራዎች ምን እንደሚመስሉ ተመልክቷል።
በተለይም ሥራውን በጀመረባቸው በአማራና አፋር ክልሎች የተፈጸሙ ወንጀሎችን የማጣራትና ወንጀለኞቹን ለፍርድ የማቅረብ ሂደት ያለበት ደረጃ በዝርዝር ታይቷል።
እስካሁን ወንጀሎች እና ወንጀሎቹ በማንና እንዴት ተፈፀሙ ከሚለው ጋር በተገናኘ በርካታ የዓይን ምስክሮችን ለማነጋገር መቻሉን እና በቂ ማስረጃ በማሰባሰብ ወንጀለኞች ላይ ክስ ለመመስረት ሂደት መጀመሩ ተገልጿል።
በሂደቱ የተገኙ ስኬቶችና እጥረቶች መዳሰሳቸውን የዘገበው ፋብኮ ነው።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“ሕዝቡ እንደቀድሞው ለመኖር የሚያስችለው የማኅበራዊ ገመድ አሁንም አለ” የማኅበራዊ ሳይንስ ምሁር
Next articleማላላ ፈንድ በአማራ ክልል የ19 ሚሊዮን ብር በላይ ፕሮጀክት ይፋ አደረገ፡፡