
አዲስ አበባ: መጋቢት 27/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የብሔራዊ አደጋ መከላከል ኮሚቴ በተፈጥሮ እና በሰው ሠራሽ አደጋዎች ለተጎዱ ወገኖች በሚደረገው የሰብዓዊ ድጋፍ አገልግሎት አሰጣጥ በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ተገምግሟል።
የብሔራዊ አደጋ መከላከል ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ደመቀ በመኮንን በአሁኑ ጊዜ መንግሥት በጦርነት እና በድርቅ በተጎዱ አካቢዎች የሚኖሩ ወገኖችን በሰብዓዊ ድጋፍ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ የሚያደርገው ሁሉአቀፍ እንቅስቃሴ የሚያበረታታ መኾኑን ገልፀዋል።
አቶ ደመቀ ችግሩ በሚስተዋልባቸው አካባቢዎች የተጀመረው እንቅስቃሴ አበረታች መኾኑን ጠቅሰው፤ ከችግሩ ውስብስብነት አኳያ የሚመጥን ፈጣን ምላሽ እና ቅንጅታዊ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ከጠላት ቁጥጥር ነፃ የወጡ አንዳንድ ኪስ ቦታዎችን በሰብዓዊ ድጋፍ አገልግሎት በፍጥነት ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል ስልት ነድፎ መንቀሳቀስ እንደሚጠይቅ ጠቁመዋል።
የፌደራል አስፈፃሚ አካላት እንደ ሀገር የገጠመንን ሰፊ እና ውስብስብ ፈተና በአጭር ጊዜ መፍትሔ ለማበጀት ቀዳሚ ትኩረት እና ክብደት ሰጥቶ በጋራ መረባረብ እንደሚገባቸው አቶ ደመቀ አስገንዝበዋል።
በሀገሪቱ የተፈጥሮ እና የሰው ሠራሽ አደጋዎች ተደራርበው መከሰታቸው እርምጃችንን ፈታኝ ቢያደርገውም፤ በተግባር ልንሻገር የሚያስችል የተናበበ ዕቅድ፣ ግልፅ አሠራር እና ውጤታማ የሃብት አጠቃቀም ስልት ተግባራዊ ማድረግ ይኖርብናል ብለዋል።
በተመሳሳይም ከሳዑዲ ተመላሽ ወገኖችን ተቀብሎ በማስተናገድ ሂደት የሚገጥሙ ችግሮችን በፍጥነት እየፈቱ በአግባቡ ከቤተሰቦቻቸው የሚቀላቀሉበትን መንገድ የጋራ ትኩረት እና ምላሽ እንዲሰጠው ጥሪ አቅርበዋል።
መረጃው የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ነው።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/