
መጋቢት 27/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ከመላው ዓለም በመሰባሰብ ዒድን በጋራ ለማክበር የቀረበው ጥሪ አንድነትና ትብብራችንን በተግባር የምናሳይበት ልዩ ታሪካዊ አጋጣሚ ነው ሲል የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ገለጸ።
ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከየትኛውም የዓለም ክፍል ለዒድ በዓል የሚመጡ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ለማስተናገድ መዘጋጀቱን አስታውቋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ ዒድን በኢትዮጵያ በታላቅ ሁኔታ ለማክበር በተደረገው ጥሪ ተደስተናል ብለዋል። ከየትኛውም የዓለም ክፍል መጥተው ዒድን አብረውን የሚያከብሩትን ኹሉ ልንቀበላቸው ተዘጋጅተናል ሲሉ ተናግረዋል።
ከመላው ዓለም በመሰባሰብ ዒድን በጋራ ለማክበር የቀረበው ጥሪ አንድነትና ትብብራችንን በተግባር የምናሳይበት ልዩ ታሪካዊ አጋጣሚ ይኾናል ያሉት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ፤ በድርቅና ጦርነት የተጎዱ ወገኖችን በመተጋገዝ ድጋፍ ለማድረግ ጥሩ አጋጣሚ እንደሚፈጠርም ገልጸዋል።
የተፈናቀሉና በተለያየ ችግር ውስጥ ያሉ ወገኖች እንደሚደገፉም ጠቁመዋል።
በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጥሪ ቀርቦላቸው በሀገራቸው ተገኝተው አብረውን ለማክበር ስለሚገኙ ኹላችንም ደስተኞች ነን ያሉት ደግሞ በምክር ቤቱ የመስጂዶችና የአውቃፍ ዘርፍ ኀላፊ ዶክተር ሸህ መሐመድ ሐሚዲን ናቸው።
በዓሉን በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው በመሰባሰብ ማክበራቸው ይበልጥ አንድነትና ወንድማማችነታቸውን የሚያሳዩበት ነው ብለዋል። በመኾኑም ለበዓሉ ድምቀትና እንግዶችን ለመቀበል ኹሉም የድርሻውን እንዲወጣ መጠየቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
በታላቁ የረመዳን ወር ሕዝበ ሙስሊሙ በመረዳዳት፣ በመተጋገዝና በመተዛዘን በፆምና የተራዊህ ሶላት በፅሞና ፈጣሪውን ለመልካም ነገር የሚለምንበት የተለየ ወር መኾኑ ይታወቃል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/