“ሕዝቡ በየደረጃው ላነሳቸው ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት ኃላፊነት ወስደን እየሠራን ነው” አቶ ግርማ የሽጥላ

215

ባሕር ዳር: መጋቢት 27/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ሕዝቡ በየደረጃው ላነሳቸው ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት በትኩረት እንደሚሠራ የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ ገልጸዋል።
አቶ ግርማ የሺጥላ እንደገለጹት ፓርቲው በመጀመሪያውና በታሪካዊው ጉባኤው የተለያዩ ሀገራዊ ውሳኔዎችን ማሳለፉን አስታውሰው የውሳኔ ሃሳቦችንም ከክልል እስከ ቀበሌ ድረስ ከመላው ሕዝብ ጋር ውይይት አድርገናል ብለዋል፡፡
አቶ ግርማ በፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች በተመራው የሕዝብ ውይይት መድረክ በርካታ ጥያቄዎች እና ተጨባጭ ችግሮች ተነስተዋል ብለዋል። በተነሱ አስተያየቶችና ችግሮች ላይ ሕዝቡ፣ ፓርቲው እና በየደረጃው ያለው የመንግሥት መዋቅር የየድርሻቸውን ኀላፊነት ወስደው የተነሱ ችግሮችን ለመፍታት በቁርጠኝነት እንደሚሠሩ በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ መግባባት እንደተፈጠረም አቶ ግርማ ገልጸዋል፡፡
አቶ ግርማ እንደገለጹት ሕዝቡ ያነሳቸውን ጥያቄዎችና ተጨባጭ ችግሮች መፍታት፣ የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ፣ ተጠያቂነትን ማዕከል ያደረገ የፓርቲ እና የመንግሥት አመራሮችን የማስፈጸም ብቃት ከፍታ በማረጋገጥ የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ፓርቲያችን ተግቶ እየሠራ ይገኛል ብለዋል፡፡
ሕዝቡ በየደረጃው ላነሳቸው ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት እየሠራን ነው ያሉት አቶ ግርማ ሥራውን ውጤታማ ለማድረግም ከሚያዝያ 1 እስከ ሰኔ 30/2014 ዓ.ም የሚቆይ የዘጠና ቀናት የአጭር ጊዜ ዕቅድ እንደተቀመጠም ገልጸዋል።
ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ከላይ እስከ ታች በየደረጃው የሚገኙ ፈጻሚ አካላት በሙሉ አቅማቸው ወደ ተጨባጭ ተግባራዊ ምላሽ እና የኅብረተሰብ ተሳትፎ፣ ተጠቃሚነት እና እርካታን ለማረጋገጥ እንደሚንቀሳቀሱ ገልጸዋል።
የፓርቲው መዋቅር ከላይ እስከ ታች በጥብቅ ዲሲፕሊንና መርህ እየተመራ የሕዝብ አስተያየት ወደ ተግባር እየተቀየሩና ጥያቄዎቹም እየተመለሱለት ስለመሆኑም በየጊዜው የመፈተሸ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚሥራ ተናግረዋል፡፡ መረጃው የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ነው።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“የህዳሴ ግድብ ግንባታ ሌሎችንም ታላላቅ ፕሮጀክቶች መሥራት እንደምንችል ያረጋገጥንበትና አቅማችን የተገነባበት የአንድነታችን ማረጋገጫ ነው” የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አነጋግረኝ ጋሻው (ዶ.ር)
Next articleMaxxansa Gaazexaa Hirkoo Guraandhala 30/2014