
መጋቢት 26/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በእስራኤል የኢፌዴሪ ኤምባሲ ባራክ ግሩፕ ከተባለው የንግድ ተቋም ጋር በመተባበር ከእስራኤል ትልቅ ከተሞች አንዷ በኾነችው የወደብ ከተማ በሃይፋ ከሚገኙ ባለሃብቶች ጋር በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንትና በንግድ ሥራዎች ያሉትን ዕድሎች በሚመለከት ምክክር አካሂዷል፡፡
በመድረኩ በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ለመሰማራት ፍላጎት ያላቸው በሃይፋ ከተማ የሚገኙ የእስራኤል የኢንዱስትሪ ባለቤቶችና፣ የንግድ ማኅበረሰብ አባላት እንዲሁም የአዳዲስ ኩባንያዎች ባለቤቶችና የሥራ ኀላፊዎች ተሳትፈዋል።
በወቅቱም በኹለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ እና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ለማሳደግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች እንዲሁም ለአዲስ ባለሀብቶች የሚሰጡ ድጋፎችን በሚመለከት ገለጻ ተደርጓል፡፡
በመድረኩ በእስራኤል የኢፌዴሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ረታ ዓለሙ በኢትዮጵያ ያለውን የኢንቨስትመንት፣ ንግድና የቱሪዝም አማራጮችን በሚመለከት ሰፊ ገለጻ አቅርበዋል። በገለጻው ኢትዮጵያ እና እስራኤል ካላቸው ጠንካራ ትስስር አንጻር የንግድና ኢንስትመንት ትብብሩን ለማጠናከር ምቹ አጋጣሚ መኖሩን ጠቅሰዋል፡፡ ባለሃብቶቹ በኢትዮጵያ እንዲሠማሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የባራክ ኩባንያ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር አርኖን ባራክ መድረክ በኢትዮጵያ በግል ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት ያላቸው በቀጣይ ከኤምባሲው ጋር የተጀመረው ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥልና በጋራ መሥራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
መድረኩ መዘጋጀቱ በኹለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የኢኮኖሚ ትብብር ከፍ ለማድረግ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ተናግረዋል፡፡ ኢንጂነር አርኖን ባራክ በኩባንያቸው የሚመራ ልዑካን ቡድን ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ያለውን ኢንቨስትመንትና የንግድ አማራጮችን ለማየት ዝግጁ መኾኑንም ገልጸዋል፡፡
በመድረኩ የተሳተፉ አካላት በኢንቨስትመንት ዘርፍ አላስፈላጊ የኾኑ የቢሮክራሲ ሂደቶችን፣ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ለመሠማራት በመንግሥት ስለሚሰጥ ድጋፍ ሐሳብ አቅርበዋል።
አምባሳደር ረታ መንግሥት በባለሃብቶች የሚነሱ ችግሮችን ለመፍታት በመዋቅር፣ በሕግ እና በአሠራር ሁኔታዎችን ለማሻሻል የወሰዳቸውን እርምጃዎች በማስረዳት መፍትሔ ለመስጠት ዝግጁ መኾኑን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ የኢኮኖሚና የሕግ ማሻሻያዎች የተደረጉ መኾኑን፣ በተለይ ትኩረት በተሰጣቸው ዘርፎች ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው የውጭ ባለሃብቶችን ለማበረታታትና አሠራሩን የተሻለ ለማድረግ የወጡትን ሕጎች በማስረጃነት በመጥቀስ ኤምባሲው ችግሮቹን ለመቅረፍ በጋራ ለመሥራት ዝግጁ እንደኾነ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com